2 ሳሙኤል 2:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ለብንያም ወገንና ለሳኦል ልጅ ለኢያቡስቴ ዐሥራ ሁለት፥ ለዳዊት ደግሞ ዐሥራ ሁለት አገልጋዮቹ ተነሥተው ተቆጠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ከብንያም ለሳኦል ልጅ ለኢያቡስቴ ዐሥራ ሁለት፣ ለዳዊት ደግሞ ዐሥራ ሁለት ሰዎች ተነሥተው ተቈጠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ከብንያም ወገን የኢያቡስቴ ተወካዮች የሚሆኑ ዐሥራ ሁለት ሰዎች ተመርጠው ከዳዊት ወገን ከተመረጡት ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጋር ውጊያ ገጠሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሳኦል ልጅ ለኢያቡስቴ ከብንያም ልጆች ዐሥራ ሁለት፥ ከዳዊትም ብላቴኖች ዐሥራ ሁለት ተቈጥረው ተነሡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለብንያም ወገንና ለሳኦል ልጅ ለኢያቡስቴ አሥራ ሁለት፥ ከዳዊትም ባሪያዎች አሥራ ሁለት ተቆጥረው ተነሡ። |
ከዚያም እያንዳንዱ ሰው የባለጋራውን ራስ ያዘ፥ ሰይፉንም በጐኑ ሻጠ፥ ተያይዘውም ወደቁ። ስለዚህም በገባዖን የሚገኘው ያ ስፍራ “የስለታም ሰይፍ ምድር” ተባለ።