ከዚያም አቤሴሎም ወደ ንጉሡ እንዲሄድለት ኢዮአብን አስጠራው፤ ኢዮአብ ግን ወደ እርሱ አልመጣም፤ ለሁለተኛ ጊዜም ላከበት፤ ኢዮአብ ግን አሁንም ሳይመጣ ቀረ።
2 ሳሙኤል 14:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ “ተመልከቱ፥ የኢዮአብ እርሻ የሚገኘው ከእኔ እርሻ አጠገብ ነው፤ በእርሻው ላይ የገብስ ሰብል አለው፤ ሄዳችሁም እሳት ልቀቁበት” አላቸው። ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች ሄደው እርሻውን በእሳት አቃጠሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ “ተመልከቱ የኢዮአብ ዕርሻ የሚገኘው ከእኔ ዕርሻ አጠገብ ነው፤ በዕርሻው ላይ የገብስ አዝመራ አለው፤ ሄዳችሁም እሳት ልቀቁበት” አላቸው። ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች ሄደው የኢዮአብን ዕርሻ በእሳት አቃጠሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም አቤሴሎም አገልጋዮቹን “ተመልከቱ፤ የኢዮአብ እርሻ ከእኔ እርሻ ቀጥሎ ሲሆን የገብስ ሰብል ይገኝበታል፤ ስለዚህም ሂዱና በእሳት አቃጥሉት” ሲል አዘዛቸው፤ እነርሱም ሄደው ሰብሉን በእሳት አቃጠሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም ብላቴኖቹን፥ “በእርሻዬ አጠገብ ያለችውን የኢዮአብን እርሻ እዩ፤ በዚያም ገብስ አለው፤ ሄዳችሁ በእሳት አቃጥሉት” አላቸው። የአቤሴሎምም ብላቴኖች እርሻውን አቃጠሉት። የኢዮአብም አሽከሮች ልብሶቻቸውን ቀድደው ተመልሰው፥ “የአቤሴሎም አሽከሮች እርሻህን በእሳት አቃጠሉት” ብለው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎቹንም፦ በእርሻዬ አጠገብ ያለውን የኢዮአብን እርሻ እዩ፥ በዚያም ገብስ አለው፥ ሂዳችሁ በእሳት አቃጥሉት አላቸው። የአቤሴሎምም ባሪያዎች እርሻውን አቃጠሉት። |
ከዚያም አቤሴሎም ወደ ንጉሡ እንዲሄድለት ኢዮአብን አስጠራው፤ ኢዮአብ ግን ወደ እርሱ አልመጣም፤ ለሁለተኛ ጊዜም ላከበት፤ ኢዮአብ ግን አሁንም ሳይመጣ ቀረ።
ኢዮአብም፥ “ከእንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከአንተ ጋር ጊዜ ማጥፋት አልችልም” አለው፤ ስለዚህ በእጁ ሦስት ጦር ይዞ ሄደና አቤሴሎም እባሉጥ ዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ ወርውሮ በልቡ ላይ ተከላቸው።
ኢዩም “ኤልዛቤልን ወደ ታች ወርውሩአት!” አላቸው፤ እነርሱም አንሥተው በወረወሩአት ጊዜ ደምዋ በግንቡና በፈረሶች ላይ ተረጨ፤ ኢዩም በሬሳዋ ላይ ፈረሶቹንና ሠረገላውን ነዳበት፤