ኦርዮም ዳዊትን፥ “ታቦቱ፥ እስራኤልና ይሁዳ በድንኳን ሆነው፥ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም ሰዎች አውላላ ሜዳ ላይ ሰፍረው፥ ለመብላትና ለመጠጣት እንዲሁም ከሚስቴ ጋር ለመተኛት እንዴት ወደ ቤቴ እሄዳለሁ? በሕይወትህና በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ይህን ነገር አላደርገውም” አለው።
2 ሳሙኤል 14:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም፥ “በዚህ ሁሉ የኢዮአብ እጅ የለበትምን?” ሲል ጠየቃት። ሴቲቱም መልሳ እንዲህ አለች፤ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ ንጉሥ ጌታዬ ከተናገረው ሁሉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም የሚል ማንም የለም። ይህን እንድናገር ያዘዘኝና ይህም ሁሉ ቃል በእኔ በአገልጋይህ አፍ ያደረገው አገልጋይህ ኢዮአብ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም፣ “በዚህ ሁሉ የኢዮአብ እጅ የለበትምን?” ሲል ጠየቃት። ሴቲቱም መልሳ እንዲህ አለች፤ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ ንጉሥ ጌታዬ ከተናገረው ሁሉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም የሚል ማንም የለም። አዎን ይህን እንዳደርግ ያዘዘኝና ይህም ሁሉ ቃል በእኔ በአገልጋይህ አንደበት እንዲነገር የላከኝ አገልጋይህ ኢዮአብ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ይህን እንድታደርጊ ያዘዘሽ ኢዮአብ ነውን?” ሲል ጠየቃት። እርስዋም እንዲህ ስትል መልስ ሰጠች፤ “ንጉሥ ሆይ! አንተ ከምትለው ሁሉ ፈጽሞ ሊወጣ የሚችል እንደሌለ በአንተ ስም እምላለሁ፤ በእርግጥም ምን ማድረግና ምን ማለት እንዳለብኝ የመከረኝ የአንተ የጦር አዛዥ የሆነው ኢዮዓብ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ “በዚህ ሁሉ ነገር የኢዮአብ እጅ ከአንቺ ጋር አለን?” አላት። ሴቲቱም ንጉሡን አለችው፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ጌታዬ ንጉሥ ከተናገረው ነገር ሁሉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሊል የሚችል የለም፤ አገልጋይህ ኢዮአብ አዝዞኛል፤ ይህንም ቃል ሁሉ በአገልጋይህ አፍ አደረገው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም፦ በዚህ ሁሉ የኢዮአብ እጅ ከአንቺ ጋር ነውን? አላት። ሴቲቱም መልሳ፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ጌታዬ ንጉሥ ከተናገረው ነገር ሁሉ ወደ ቀኝ ወደ ግራም ሊል የሚችል የለም፥ ባሪያህ ኢዮአብ አዝዞኛል፥ ይህንም ቃል ሁሉ በባሪያህ አፍ አደረገው። |
ኦርዮም ዳዊትን፥ “ታቦቱ፥ እስራኤልና ይሁዳ በድንኳን ሆነው፥ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም ሰዎች አውላላ ሜዳ ላይ ሰፍረው፥ ለመብላትና ለመጠጣት እንዲሁም ከሚስቴ ጋር ለመተኛት እንዴት ወደ ቤቴ እሄዳለሁ? በሕይወትህና በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ይህን ነገር አላደርገውም” አለው።
በሌላ በኩል ደግሞ በነፍሴ ቆርጬ ሕይወቱን ባጠፋው ኖሮ፥ ከንጉሡ ተደብቆ የሚቀር ነገር ስለ ሌለ፥ አንተም ራስህ በተነሣህብኝ ነበር” ብሎ መለሰለት።
አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፥ ኢዮአብ ለብቻው የሚያነጋግረው በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።
ደሙ በኢዮአብ ራስና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይሁን፤ ከኢዮአብ ቤት ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ወይም የሥጋ ደዌ ያለበት፥ በምርኲዝ የሚሄድ አንካሳ፥ ወይም በሰይፍ ተመቶ የሚሞት ወይም የሚበላው ያጣ ራብተኛ አይታጣ።”
“አበኔር እንደ ተራ ሰው ይሙት? እግሮችህ በእግር ብረት አልገቡም፤ ሰው በክፉ ሰዎች ፊት እንደሚወድቅ አንተም እንደዚሁ ወደቅህ።” ሕዝቡም ሁሉ እንደገና አለቀሱለት።
በመንገድም ሳሉ ኤልያስ ኤልሳዕን “እነሆ፥ አንተ በዚህ ቆይ፤ እኔ ወደ ቤትኤል እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ ከቶ ከአንተ አልለይም” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ወደ ቤትኤል ሄዱ።
እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ፥ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፥ ከጉድጓዶችም ውኃን አንጠጣም፤ በንጉሡ ጐዳና እንሄዳለን፥ ግዛትህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።”
ነገር ግን ጽና፥ እጅግም በርታ፤ ባርያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ከእርሱ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።
ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ለመግጠም ሲሄድ ሳኦል ተመልክቶ የሠራዊቱን አዛዥ አበኔርን፥ “አበኔር ሆይ፤ ይህ ልጅ የማን ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም፥ “ንጉሥ ሆይ፤ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ አላውቅም” ብሎ መለሰለት።
ዳዊት ግን፥ “በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አባትህ በሚገባ ያውቃል፤ እርሱም በልቡ፤ ‘ዮናታን እንዳያዝን ይህን ማወቅ የለበትም’ ብሏል፤ ነገር ግን ሕያው ጌታን! በነፍስህ እምላለሁ! በእኔና በሞት መካከል አንድ እርምጃ ብቻ ቀርቷል” ብሎ ማለ።
ጌታዬ ሆይ፤ በሕያው ጌታ፥ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ ደም ከማፍሰስና በገዛ እጅህ ከመበቀል የጠበቀህ ጌታ ነው፤ አሁንም ጠላቶችህና ጌታዬን ሊጐዱ የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ፤