ከዚያም ናታን፥ ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ያ ሰው አንተ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ የሚለው ይህን ነው፤ ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ፤ ከሳኦልም እጅ ታደግሁህ፤
2 ሳሙኤል 14:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቲቱም እንዲህ አለችው፥ “አንተስ እንዲህ ያለውን ነገር በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ያሰብኸው ለምንድን ነው? ከአገር የተሰደደውን ልጁን ንጉሡ ባለመመለሱ፥ ይህን ሲናገር በራሱ ላይ መፍረዱ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴቲቱም መልሳ እንዲህ አለችው፣ “እንዲህ ያለውን ነገር በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ያሰብኸው ለምንድን ነው? ንጉሡ ከአገር የተሰደደውን ልጁን አልመለሰውም፤ ታዲያ ይህን ሲናገር በራሱ ላይ መፍረዱ አይደለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም እንዲህ አለችው፤ “በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ይህን የመሰለ በደል የፈጸምከው ስለምንድን ነው? ልጅህ ከተሰደደበት አገር ተመልሶ እንዲመጣ አልፈቀድክለትም፤ ስለዚህ አሁን በተናገርከው ቃል በራስህ ላይ ፈርደሃል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም አለች፥ “በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ እንዲህ ያለ ነገር ስለምን አሰብህ? ወይስ ንጉሥ ያሳደደውን ስላላስመለሰ እንደ በደል ከንጉሥ አፍ ይህ ቃል ወጥቶአልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም አለች፦ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ እንዲህ ያለ ነገር ስለምን አሰብህ? ንጉሡ ይህን ነገር ተናግሮአልና ያሳደደውን ስላላስመለሰ በደለኛ ነው። |
ከዚያም ናታን፥ ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ያ ሰው አንተ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ የሚለው ይህን ነው፤ ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ፤ ከሳኦልም እጅ ታደግሁህ፤
አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፤ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ እንድትሆን ከሜዳ አነሣሁህ፤ ከበግ ጥበቃም ወሰድሁህ፤
የእስራኤል ሕዝብ ነገዶች ሁሉ ቁጥራቸው አራት መቶ ሺህ በሚሆን፥ ሰይፍ በሚመዙ እግረኞች ወታደሮች በሆኑ በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ መካከል ተገኙ።