ነቢዩ ኤልሳዕ በብርቱ ደዌ ታሞ ነበር፤ ተኝቶም ሊሞት በሚያጣጥርበት ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ሄዶ፥ ድምፁን ከፍ በማድረግ “አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ! አንተ እኮ የእስራኤል ሕዝብ ኀይላቸውና ጋሻ መከታቸው ነህ!” እያለ አለቀሰለት።
2 ነገሥት 6:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ንጉሥ ሶርያውያንን ባያቸው ጊዜ “ጌታዬ ሆይ! ልግደላቸውን? ልግደላቸውን?” ሲል ኤልሳዕን ጠየቀው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤልም ንጉሥ ባያቸው ጊዜ፣ “አባቴ ሆይ፤ ልግደላቸውን? ልፍጃቸውን?” ብሎ ኤልሳዕን ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤልም ንጉሥ ሶርያውያንን ባያቸው ጊዜ “ጌታዬ ሆይ! ልግደላቸውን? ልግደላቸውን?” ሲል ኤልሳዕን ጠየቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ንጉሥ ባያቸው ጊዜ ኤልሳዕን፥ “አባቴ ሆይ፥ ልግደላቸውን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ንጉሥ ባያቸው ጊዜ አልሳዕን “አባቴ ሆይ! ልግደላቸውን? ልግደላቸውን?” አለው። |
ነቢዩ ኤልሳዕ በብርቱ ደዌ ታሞ ነበር፤ ተኝቶም ሊሞት በሚያጣጥርበት ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ሄዶ፥ ድምፁን ከፍ በማድረግ “አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ! አንተ እኮ የእስራኤል ሕዝብ ኀይላቸውና ጋሻ መከታቸው ነህ!” እያለ አለቀሰለት።
ኤልሳዕም ይህን ሁሉ እያየ “የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች የሆንክ አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ!” እያለ ወደ ኤልያስ ጮኸ፤ ከዚያም በኋላ ኤልያስን ዳግመኛ አላየውም። ኤልሳዕም ከኀዘን ብዛት የተነሣ ልብሱን ከሁለት ቀደደ፤
የንዕማንም አሽከሮች ወደ እርሱ ቀረብ ብለው፥ “ጌታችን ሆይ፥ ነቢዩ ሌላ ከባድ ነገር እንድታደርግ ቢያዝህ ኖሮ ትፈጽመው ነበር፤ ታዲያ ነቢዩ ባዘዘህ መሠረት ታጥበህ ከበሽታህ መንጻት ምን ይከብድሃል?” አሉት።
ስለዚህም አዛሄል በደማስቆ ከሚገኘው ምርጥ የምድር በረከት ሁሉ በአርባ ግመሎች ጭኖ ወደ ኤልሳዕ ሄደ፤ አዛሄልም ኤልሳዕን ባገኘው ጊዜ “ልጅህ ንጉሥ ቤንሀዳድ ከሕመሙ ይድን ወይም አይድን እንደሆነ እንድትነግረው እጠይቅህ ዘንድ ልኮኛል” አለው።
ሳኦልም በመንገድ ዳር ወዳለው ወደ አንድ የበጎች ማደሪያ በደረሰ ጊዜ፥ ዋሻ አግኝቶ ወገቡን ሊሞክር ወደዚያ ገባ። ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር።
አቢሳም ዳዊትን፥ “ዛሬ እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ ላይ ጥሎታል፤ አሁንም እኔ አንድ ጊዜ በጦር ወግቼ ከመሬት ጋር ላጣብቀው፤ መድገምም አያስፈልገኝም” አለው።