2 ነገሥት 4:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የልጁ እናት ግን ኤልሳዕን “በምተማመንበት በሕያው እግዚአብሔር ስምና በነፍስህ እምላለሁ፤ ከቶ አንተን ትቼ አልሄድም!” አለችው፤ ስለዚህ እርሷን ተከትሎ ለመሄድ ተነሣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልጁ እናት ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን፤ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፣ ፈጽሞ ትቼህ አልሄድም” አለችው፤ ስለዚህ ተነሥቶ ተከተላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የልጁ እናት ግን ኤልሳዕን “በምተማመንበት በሕያው እግዚአብሔር ስምና በነፍስህ እምላለሁ፤ ከቶ አንተን ትቼ አልሄድም!” አለችው፤ ስለዚህ እርስዋን ተከትሎ ለመሄድ ተነሣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሕፃኑም እናት፥ “ሕያው እግዚአብሔርን! ሕያው ነፍስህንም! አልተውህም” አለች፤ ኤልሳዕም ተነሥቶ ተከተላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሕፃኑም እናት “ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ! አልተውህም፤” አለች፤ ተነሥቶም ተከተላት። |
በመንገድም ሳሉ ኤልያስ ኤልሳዕን “እነሆ፥ አንተ በዚህ ቆይ፤ እኔ ወደ ቤትኤል እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ ከቶ ከአንተ አልለይም” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ወደ ቤትኤል ሄዱ።
ከዚህም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን፥ “እነሆ! አንተ በዚህ ቆይ፤ እኔ ወደ ኢያሪኮ እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ! ከቶ ከአንተ አልለይም!” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ወደ ኢያሪኮ ሄዱ።
ከዚህም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን፥ “እነሆ! አንተ በዚህ ቆይ፤ እኔ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ! ከቶ ከአንተ አልለይም!” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ጉዞአቸውን ቀጠሉ።