በዕድሜህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምርልሃለሁ፤ አንተንና ይህችን የኢየሩሳሌምን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ በመታደግ አድናለሁ፤ ስለ ክብሬና ለአገልጋዬ ለዳዊት ስለ ሰጠሁት የተስፋ ቃል ከተማይቱን በመከላከል እጠብቃታለሁ።’”
2 ነገሥት 20:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ኢሳይያስ የንጉሡን አገልጋዮች፥ “የበለስ ፍሬ ጥፍጥፍ አምጡልኝ” ብሎ አመጡለት፤ በቁስሉ ላይ ባደረጉለት ጊዜ የሕዝቅያስ ቁስል ተፈወሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢሳይያስ፣ “ትኵስ የበለስ ጥፍጥፍ አዘጋጁ” አላቸው፤ እነርሱም አዘጋጅተው ዕባጩ ላይ አደረጉለት፤ ተፈወሰም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢሳይያስ የንጉሡን አገልጋዮች፥ “የበለስ ፍሬ ጥፍጥፍ አምጡልኝ” ብሎ አመጡለት፤ በቊስሉ ላይ ባደረጉለት ጊዜ የሕዝቅያስ ቊስል ተፈወሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢሳይያስም አለው፥ “የበለስ ጥፍጥፍ አምጥተህ በእባጭህ ላይ አድርግ ትፈወሳለህም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢሳይስም “የበለስ ጥፍጥፍ አምጡልኝ፤” አለ፤ አምጥተውም በእባጩ ላይ አደርጉለት፤ እርሱም ተፈወሰ። |
በዕድሜህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምርልሃለሁ፤ አንተንና ይህችን የኢየሩሳሌምን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ በመታደግ አድናለሁ፤ ስለ ክብሬና ለአገልጋዬ ለዳዊት ስለ ሰጠሁት የተስፋ ቃል ከተማይቱን በመከላከል እጠብቃታለሁ።’”
ንጉሥ ሕዝቅያስም ኢሳይያስን “እግዚአብሔር እንደሚፈውሰኝና ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ መሄድ እንደምችል በምን ምልክት ዐውቃለሁ?” ሲል ጠየቀው።
ኤልሳዕም ዱቄት እንዲሰጡት ጠይቆ በድስቱ ውስጥ ጨመረውና “ወጡን እያወጣህ ጨምርላቸው” ሲል አዘዘ፤ በዚህም ጊዜ በወጡ ውስጥ ምንም ዓይነት መራራነት አልነበረም።