2 ነገሥት 18:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቅያስ ‘በእግዚአብሔር ታመኑ፤ እርሱ ያድናችኋል፤ ከተማችንም በአሦርያውያን ሠራዊት እጅ እንዳትገባ ይከላከልልናል’ እያለ የሚሰብካችሁን አትስሙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ሕዝቅያስ፣ ‘እግዚአብሔር በርግጥ ያድነናል፤ ይህች ከተማ ለአሦር ንጉሥ ዐልፋ አትሰጥም’ እያለ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቅያስ ‘በእግዚአብሔር ታመኑ፤ እርሱ ያድናችኋል፤ ከተማችንም በአሦርያውያን ሠራዊት እጅ እንዳትገባ ይከላከልልናል’ እያለ የሚሰብካችሁን አትስሙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቅያስም፦ እግዚአብሔር በእርግጥ ያድነናል፤ ይህችንም ከተማ የአሦር ንጉሥ ሊይዛት አይችልም እያለ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቅያስም “እግዚአብሔር በእርግጥ ያድነናል፤ ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም፤” ብሎ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ። |
ሕዝቅያስ የሚላችሁን አታዳምጡ፤ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ከከተማችሁ ወጥታችሁ እጃችሁን እንድትሰጡ አዞአችኋል፤ ይህን ብታደርጉ ሁላችሁም እያንዳንዳችሁ የወይን ተክሎቻችሁን ዘለላና የበለስ ዛፎቻችሁን ፍሬ ትበላላችሁ፤ ከጉድጓዶቻችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ፤
የሰደብከውና የተዳፈርከው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው በማን ላይ ነው? በትዕቢትስ ዐይንህን ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ ነው።
ኢሳይያስ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብላችሁ ለጌታችሁ ንገሩት አላቸው፤ ‘የአሦር ንጉሥ አገልጋዮች ሲሰድቡኝ ስለ ሰማችሁት ቃል አትፍሩአቸው።
ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር። መኰንኖቹም “ሌሎችን አዳነ፤ እርሱ በእግዚአብሔር የተመረጠው ክርስቶስ ከሆነ፥ ራሱን ያድን፤” እያሉ ያፌዙበት ነበር።