La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 15:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዖዝያ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዳግማዊ ኢዮርብዓም ልጅ ዘካርያስ በእስራኤል ነገሠ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ ስድስት ወር ገዛ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የይሁዳ ንጉሥ ዓዛርያስ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት፣ የኢዮርብዓም ልጅ ዘካርያስ በሰማርያ ከተማ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ስድስት ወርም ገዛ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዖዝያ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዳግማዊ ኢዮርብዓም ልጅ ዘካርያስ በእስራኤል ነገሠ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ ስድስት ወር ገዛ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በዓ​ዛ​ር​ያስ በሠ​ላሳ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ልጅ ዘካ​ር​ያስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ስድ​ስት ወር ነገሠ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በይሁዳ ንጉሥ በዓዛርያስ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የኢዮርብዓም ልጅ ዘካርያስ በእስራኤል ላይ በሰማርያ ስድስት ወር ነገሠ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 15:8
14 Referencias Cruzadas  

ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ኢዩን “በአክዓብ ተወላጆች ሁሉ ላይ ልታደርግ የሚገባህን ባዘዝኩህ መሠረት ፈጽመሃል፤ ከዚህም የተነሣ የአንተ ትውልድ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ላይ እንደሚነግሡ የተስፋ ቃል እሰጥሃለሁ” አለው።


የይሁዳም ሕዝብ ዐሥራ ስድስት ዓመት ዕድሜ የነበረውን ልጁን ዖዝያን አነገሡ፤


ከዚህ በኋላ ዳግማዊ ኢዮርብዓም ሞተ፤ በነገሥታት መካነ መቃብርም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ዘካርያስ ነገሠ።


ዳግማዊ ኢዮርብዓም በእስራኤል በነገሠ በሀያ ሰባተኛው ዓመት የአሜስያስ ልጅ ዖዝያ በይሁዳ ንጉሥ ሆነ፤


ዖዝያ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት የያቤሽ ልጅ ሻሉም የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ አንድ ወር ብቻ ገዛ።


ዖዝያ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት የጋዲ ልጅ ምናሔም በእስራኤል ነገሠ፤ መኖሪያውን በሰማርያ አድርጎ ዐሥር ዓመት ገዛ።


ዖዝያ በይሁዳ በነገሠ በኀምሳኛው ዓመት የምናሔም ልጅ ፈቃሕያ በእስራኤል ነገሠ፤ መኖርያውንም በሰማርያ አድርጎ ሁለት ዓመት ገዛ፤


ዖዝያ ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በቀድሞ አባቶቹ መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢዮአታም ነገሠ።


እርሱም ከእርሱ በፊት እንደነበሩት ነገሥታት ሁሉ ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ እንዲሁም እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት ተከተለ፤


አገሪቱ ዓመፀኛ ስትሆን መሪዎችዋ ብዙ ሆኑ፥ በአስተዋይና በአዋቂ ሰው ግን ዘመንዋ ይረዝማል።


ጌታም እንዲህ አለው፦ “ከጥቂት ዘመን በኋላ የኢይዝራኤልን ደም በኢዩ ቤት ላይ እበቀላለሁና፥ ከእስራኤልም ቤት መንግሥትን እሽራለሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው፤


የይስሐቅም የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፥ የእስራኤልም መቅደሶች ባድማ ይሆናሉ፤ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፍ እነሣለሁ።”