La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 15:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ ንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነትን በመከተል ኃጢአት ስለ ሠራ እግዚአብሔርን አሳዘነ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤልን ካሳተበት ኀጢአት አልተመለሰም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ ንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነትን በመከተል ኃጢአት ስለ ሠራ እግዚአብሔርን አሳዘነ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አ​ትም አል​ራ​ቀም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ እስራኤልን ካሳተው ከናባጥ ልጅ ከኢዮርብዓም ኀጢአት አልራቀም።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 15:28
8 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ አካዝያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።


እርሱም ከእርሱ በፊት እንደነበረው እንደ ንጉሥ ኢዮርብዓም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ እስራኤልንም ወደ ኃጢአት መራ፤ ከክፉ ሥራውም ከቶ አልተገታም።


ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ኢዮርብዓም እስራኤልን ወደ ኃጢአት ከመራበት ከበደል ሥራቸው አልተመለሱም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ በኃጢአታቸው ጸንተው አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስል በሰማርያ ማምለክ ቀጠሉ።


እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት በመሥራቱም እግዚአብሔርን አሳዘነ።


ዖዝያ በይሁዳ በነገሠ በኃምሳ ሁለተኛው ዓመት የረማልያ ልጅ ፈቁሔ በእስራኤል ነገሠ፤ መኖርያውንም በሰማርያ አድርጎ ሀያ ዓመት ገዛ።


የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር ዒዮን፥ አቤልቤትማዕካ፥ ያኖሐ፥ ቄዴሽና ሐጾር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች፥ እንዲሁም የገለዓድን፥ የገሊላንና የንፍታሌምን ግዛቶች በመውረር ሕዝቡን ወደ አሦር ማርኮ የወሰደውም ይኸው ፋቁሔ በነገሠበት ዘመን ነበር።


እርሱም ከእርሱ በፊት እንደነበሩት ነገሥታት ሁሉ ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ እንዲሁም እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት ተከተለ፤


እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ አገር በሚገቡበት ጊዜ እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋቸውን የአሕዛብን አሳፋሪ ልማድ በመከተል ምናሴ የሠራው ኃጢአት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤