2 ነገሥት 14:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳግማዊ ኢዮርብዓምም እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ ከእርሱ በፊት የነበረውን የናባጥ ልጅ የኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤልን ካሳተበት ኀጢአት አልተመለሰም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳግማዊ ኢዮርብዓምም እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ ከእርሱ በፊት የነበረውን የናባጥ ልጅ የኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ነገር አደረገ እስራኤልንም ካሳታቸው ከናባጥ ልጅ ከኢዮርብዓም ኀጢአት ሁሉ አልራቀም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ እስራኤልንም ካሳተው ከናባጥ ልጅ ከኢዮርብዓም ኀጢአት ሁሉ አልራቀም። |
አንተም ቀድሞ እንደጠፋብህ ሠራዊት፥ ፈረሱን በፈረስ ፋንታ፥ ሠረገላውንም በሠረገላ ፋንታ፥ ሠራዊትን ቁጠር፥ በሜዳም ላይ ከእነርሱ ጋር እንዋጋለን፥ በእርግጥም እንበረታባቸዋለን።” ምክራቸውንም ሰማ፥ እንዲሁም አደረገ።
እርሱም ከእርሱ በፊት እንደነበረው እንደ ንጉሥ ኢዮርብዓም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ እስራኤልንም ወደ ኃጢአት መራ፤ ከክፉ ሥራውም ከቶ አልተገታም።
ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ኢዮርብዓም እስራኤልን ወደ ኃጢአት ከመራበት ከበደል ሥራቸው አልተመለሱም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ በኃጢአታቸው ጸንተው አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስል በሰማርያ ማምለክ ቀጠሉ።
የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ እርሱም መኖሪያውን በሰማርያ አድርጎ አርባ አንድ ዓመት ገዛ።
ቀድሞ የእስራኤል ይዞታ የነበረውን በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ ጀምሮ በስተ ደቡብ እስከ ሙት ባሕር የሚገኘውን ግዛት ሁሉ ድል ነሥቶ እንደገና አስመለሰ፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው በጋትሔፌር ተወላጅ አገልጋይ በሆነው በአሚታይ ልጅ በነቢዩ ዮናስ አማካይነት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነው።
የገዛ ልጁንም መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እርሱም ራሱ ሟርተኛና አስማተኛ ሆኖ ከጠንቋዮችና ከሙታን ጠሪዎች ምክርን ይጠይቅ ነበር፤ በዚህም ሁሉ አድራጎቱ ታላቅ ኃጢአት በመሥራቱ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሣ።
የቤቴልም ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም እንዲህ ብሎ ላከ፦ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል አሢሮብሃል፤ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም።
ከዚህም በኋላ እንደገና አርባ ቀንና አርባ ሌሊት እህል ሳልቀምስና ውኃ ሳልጠጣ በጌታ ፊት በግንባሬ ተደፍቼ ቆየሁ። ይህንንም ያደረግኹት ስለ ሠራችሁት ኃጢአት ሁሉ፥ እርሱንም ለማስቆጣት በጌታ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ስላደረጋችሁ ነበር።