እነርሱም ስለ እኔ ነፍስ ሲሉ አንገታቸውን አደጋ ላይ ጣሉ፤ እነርሱንም እኔ ብቻ ሳልሆን የአሕዛብም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያመሰግኗቸዋል፤
2 ቆሮንቶስ 8:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም ጋር ስለ ወንጌል ስብከት በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም እንልካለን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱም ጋራ በወንጌል ስብከት በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም ልከነዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በወንጌል ስብከቱ በአብያተ ክርስቲያን ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም ከእርሱ ጋር እንልካለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ወንጌል ትምህርት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያመሰገኑትን ወንድማችንንም ከእርሱ ጋር ልከናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም ጋር ስለ ወንጌል ስብከት በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም እንልካለን፤ |
እነርሱም ስለ እኔ ነፍስ ሲሉ አንገታቸውን አደጋ ላይ ጣሉ፤ እነርሱንም እኔ ብቻ ሳልሆን የአሕዛብም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያመሰግኗቸዋል፤
በዚህ ምክንያት የተወደደውንና የታመነውን በጌታ ልጄ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ፤ በየስፍራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እኔ እንደማስተምረው በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነው መንገዴን እርሱ ያሳስባችኋል።
ቲቶን ገፋፋሁት፤ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ላክሁት፤ ቲቶስ ለራሱ ጥቅም አውሏችኋልን? በአንድ መንፈስ አልተመላለስንምን? አንድ ዓይነት እርምጃስ አልወሰድንምን?
ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የጌታን የራሱን ክብርና የእኛን በጎ ፈቃድ ለማሳየት በምናገለግለው በዚህ የቸርነት ሥራ ከእኛ ጋር አብሮን እንዲሄድ በአብያተ ክርስቲያናት ተመርጧል።