ከእስራኤል ልጆች ርስት ለሌዋውያን የምትሰጡአቸውን ከተሞች እንዲሁ ስጡ፤ ከብዙዎቹ ብዙ፥ ከጥቂቶቹ ጥቂት ትወስዳላችሁ፤ እያንዳንዱ እንደ ወረሱት እንደ ርስታቸው መጠን ከከተሞቻቸው ለሌዋውያን ይሰጣሉ።”
2 ቆሮንቶስ 8:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በናንተ ላይ ጫና ይብዛ ለሌሎች ደግሞ ዕረፍት ይሁን ማለቴ አይደለም፤ ነገር ግን ሁላችሁም እኩል እንድትሆኑ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን የምንለው እናንተ ተቸግራችሁ ሌሎች ይድላቸው ለማለት ሳይሆን፣ ሁላችሁም እኩል እንድትሆኑ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ስል ሁላችሁም እኩል እንድትሆኑ እንጂ እናንተ በመስጠት ስትቸገሩ ሌሎች እንዲያርፉ ብዬ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህ ወራት ተካክላችሁ እንድትኖሩ ነው እንጂ ሌላው እንዲያርፍ እናንተን የምናስጨንቅ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሌሎች ዕረፍት ለእናንተም መከራ እንዲሆን አይደለም፥ ትክክል እንዲሆን ነው እንጂ፤ |
ከእስራኤል ልጆች ርስት ለሌዋውያን የምትሰጡአቸውን ከተሞች እንዲሁ ስጡ፤ ከብዙዎቹ ብዙ፥ ከጥቂቶቹ ጥቂት ትወስዳላችሁ፤ እያንዳንዱ እንደ ወረሱት እንደ ርስታቸው መጠን ከከተሞቻቸው ለሌዋውያን ይሰጣሉ።”