La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ቆሮንቶስ 4:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን እንዲገለጥ፥ እኛ ሕያዋን የሆንን ስለ ኢየሱስ ስንል ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የኢየሱስ ሕይወት ሟች በሆነው ሥጋችን እንዲገለጥ፣ እኛ ሕያዋን የሆንን ሁልጊዜ ስለ ኢየሱስ ለሞት ዐልፈን እንሰጣለንና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የኢየሱስ ሕይወት በሟች ሰውነታችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋኑ ስለ ኢየሱስ ሁልጊዜ ለሞት ተላልፈን እንሰጣለን።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሕ​ይ​ወት የም​ን​ኖር እኛም በሟች ሰው​ነ​ታ​ችን ላይ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሕይ​ወቱ ይገ​ለጥ ዘንድ፥ ዘወ​ትር ስለ ኢየ​ሱስ ክስ​ር​ቶስ ብለን ተላ​ል​ፈን ለሞት እን​ሰ​ጣ​ለን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና።

Ver Capítulo



2 ቆሮንቶስ 4:11
11 Referencias Cruzadas  

በምድር ላይ እንደ ተሰነጠቀ እንደ መሬት ጓል፥ እንዲሁ አጥንቶቻችን በሲኦል ተበተኑ።


እግዚአብሔር ይህንን አይመረምርም ነበርን? እርሱ ልብ የሰወረውን ያውቃልና።


ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው መንፈስ በእናንተ የሚኖር ከሆነ፥ ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው መንፈስ፥ በውስጣችሁ በሚኖረው በመንፈሱ አማካይነት፥ ለሟች አካላቶቻችሁ ሕይወትን ይሰጠዋል።


ይህም “ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።


ወንድሞች ሆይ፤ እኔ በየቀኑ እሞታለሁ፤ ይህንንም በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ በእናንተ ላይ ባለኝ ትምክህት አረጋግጣለሁ።


የምድራዊውን ሰው መልክ እንደለበስን፥ የሰማያዊውን ሰው መልክ ደግሞ እንለብሳለን።


የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን እንዲገለጥ፥ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን።


ስለዚህ ሞት በእኛ፥ ሕይወት ግን በእናንተ ይሠራል።


በእውነትም የሚሞተው በሕይወት እንዲዋጥ፥ ጨምረን ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ የማንወድ ስለሆነ፥ በዚህ ድንኳን ሳለን ከብዶን እንቃትታለን።


ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤