2 ቆሮንቶስ 13:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተ ርቄ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ሥልጣኔን በኃይል እንዳልጠቀም ነው፤ ጌታም ይህን ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተ ርቄ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ሥልጣኔን በኀይል እንዳልጠቀም ነው፤ ጌታም ይህን ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን መልእክት ከእናንተ ርቄ ሳለሁ የጻፍኩላችሁ በዚሁ ምክንያት ነው፤ በዚህ ዐይነት ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ጌታም በሰጠኝ ሥልጣን አላስጨንቃችሁም፤ ጌታ ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ እናንተን ለማፍረስ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም እግዚአብሔር ለማፍረስ ያይደለ ለማነጽ በሰጠን ሥልጣን ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ ቍርጥ ነገር እንዳላደርግባችሁ፥ ሥልጣን እንዳለው ሰው ከእናንተ ጋር ሳልኖር ይህን እጽፋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ጌታ ለማፍረስ ያይደለ ለማነጽ እንደ ሰጠኝ ሥልጣን፥ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በቁርጥ እንዳልሠራ በሩቅ ሆኜ ይህን እጽፋለሁ። |
ስመጣ ግን በዓለማዊ ልማድ እንደምንመላለስ በሚቆጥሩን በአንዳንዶች ላይ በድፍረት ለመናገር አስባለሁ፤ እናንተን ግን በዚያ ድፍረት እንድናገር እንዳታደርጉኝ እለምናችኋለሁ።
ለሁለተኛ ጊዜ ከእናንተ ጋር በነበርሁ ጊዜ እንደነገርኳችሁ አሁንም ደግሞ በሩቅ ስሆን፥ እንደገና ብመጣ እንዳልራራላቸው አስቀድመው ኃጢአት ለሠሩት ለሌሎችም ሁሉ አስቀድሜ እናገራለሁ፤