2 ዜና መዋዕል 9:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡንም እንዲህ አለችው፦ “ስለ ስኬትህና ስለ ጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ዝና እውነት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡንም እንዲህ አለችው፤ “ስለ ተናገርሃቸው ነገሮችና ስለ ጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት እውነት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሰሎሞንንም እንዲህ አለችው “ስለ አንተ ሥራና ስለ ጥበብህ ታላቅነት በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ሁሉ እውነት ነው! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡንም አለችው፥ “ስለ ነገርህና ስለ ጥበብህ በሀገሬ ሳለሁ የሰማሁት ዝና እውነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡንም አለችው “ስለ ነገርህና ስለ ጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ዝና እውነት ነው። |
የማዕዱንም መብል፥ የሹማምንቱንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም አሠራር አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም አለባበሳቸውንም፥ በጌታም ቤት የሚያሳርገውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ እጅግ ተደነቀች።
እኔ ግን መጥቼ በዓይኔ እስካየሁ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም፤ እነሆ፥ የጥበብህን ታላቅነት እኩሌታ አልነገሩኝም፤ ከሰማሁት ዝና ትበልጣለህ።