2 ዜና መዋዕል 9:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዙፋኑም ጋር ተጋጥመው ወደ ዙፋኑም የሚያስኬዱ ስድስት እርከኖችና የወርቅ ብርኩማ ዙፋኑ ነበረው፤ በዚህና በዚያም በመቀመጫው አጠገብ ሁለት የክንድ መደገፊያዎች ነበሩበት፥ በመደገፊያዎችም አጠገብ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዙፋኑ ባለስድስት ደረጃ ሲሆን፣ ከዙፋኑ ጋራ የተያያዘ ከወርቅ የተሠራ የእግር መርገጫ ነበረው። መቀመጫውም ግራና ቀኙ መደገፊያ ያለው ሲሆን፣ በመደገፊያዎቹም አጠገብ ሁለት አንበሶች ቆመዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዙፋኑም ከታች ወደ ላይ መወጣጫ የሆኑ ስድስት ደረጃዎች ነበሩት፤ በእያንዳንዱም ደረጃ ጫፍ በግራና በቀኝ አንዳንድ የአንበሳ ምስል ሲኖር በድምሩ የተቀረጹት የአንበሳ ምስሎች ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ከዙፋኑ ጋር ተያይዞ ከወርቅ የተሠራ የእግር መረገጫም ነበረው፤ በሁለቱ የክንድ መደገፊያ ጫፎችም ላይ አንዳንድ የአንበሳ ምስል ነበር፤ በሌላ በየትኛውም አገር መንግሥት ይህን የመሰለ ዙፋን ከቶ አልነበረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ዙፋኑም የሚያስሄዱ፥ በወርቅ የተለበጡ ስድስት እርከኖች ነበሩ፤ በዚህና በዚያ በመቀመጫው አጠገብ ሁለት የክንድ መደገፊያዎች ነበሩበት፤ በመደገፊያዎቹም አጠገብ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዙፋኑም ጋር ተጋጥመው ወደ ዙፋኑም የሚያስሄዱ ስድስት እርከኖች ነበሩ፤ የወርቅ ብርኩማም ነበረ፤ በዚህና በዚያም በመቀመጫው አጠገብ ሁለት የክንድ መደገፊያዎች ነበሩበት፤ በመደገፊያዎችም አጠገብ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር። |
እንደ አንበሳ ዐርፎ ተኝቶአል፥ እንደ እንስቲቱም አንበሳ ተጋድሞአል፤ ማን ያስነሣዋል? የሚባርክህ ሁሉ የተባረከ ይሁን፥ የሚረግምህም ሁሉ የተረገመ ይሁን።”
ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።