2 ዜና መዋዕል 6:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ከአብራክህ የተገኘው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤትን ይሠራል እንጂ ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ቤተ መቅደሱን የምትሠራው አንተ አይደለህም፤ ለስሜ ቤተ መቅደስ የሚሠራልኝ ከአብራክህ የሚከፈለው፣ የገዛ ልጅህ ነው።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን ቤተ መቅደስን የሚሠራልኝ ከአብራክህ የተገኘ የአንተው የራስህ ልጅ እንጂ አንተ አይደለህም’ አለው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ከወገብህ የሚወጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤትን ይሠራል እንጂ አንተ አትሠራልኝም አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከወገብህ የሚወጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤትን ይሠራል እንጂ ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም፤’ አለው። |
ጌታም የተናገረውን ቃል ፈጸመ፤ ጌታም ተስፋ እንደሰጠ በአባቴ በዳዊት ፋንታ ተነሣሁ፥ በእስራኤልም ዙፋን ላይ ተቀመጥሁ፥ ለእስራኤልም አምላክ ለጌታ ስም ቤት ሠራሁ።