እርሱንም ኒካዑ ተብሎ የሚጠራው የግብጽ ንጉሥ ኢዮአካዝ በኢየሩሳሌም እንዳይነግሥ በሐማት ምድር በምትገኘው በሪብላ እስረኛ በማድረግ፥ ይሁዳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ብር፥ ሠላሳ አራት ኪሎ ወርቅ ግብር እንዲከፍል ባደረገው ጊዜ የኢዮአካዝ ዘመነ መንግሥት ፍጻሜ ሆነ።
2 ዜና መዋዕል 36:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የግብጽም ንጉሥ ከኢየሩሳሌም ከመንግሥቱ አወረደው፥ በምድሪቱም በሚኖሩት ላይ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ግብር ጣለባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የግብጽ ንጉሥ በኢየሩሳሌም ካለው ዙፋኑ አወረደው፣ በአገሩም ላይ አንድ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ግብር ጣለበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግብጽ ንጉሥ ኒካዑ ኢዮአሐዝን እስረኛ አድርጎ ወሰደው፤ የይሁዳንም ሕዝብ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ የሚመዝን ብርና ሠላሳ አራት ኪሎ የሚመዝን ወርቅ እንዲገብርለት አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ወደ ግብፅ ወሰደው፤ በሀገሩም ላይ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ግብር ጣለበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የግብጽም ንጉሥ በኢየሩሳሌም ከመንግሥቱ አወጣው፤ መቶም መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ዕዳ ጣለበት። |
እርሱንም ኒካዑ ተብሎ የሚጠራው የግብጽ ንጉሥ ኢዮአካዝ በኢየሩሳሌም እንዳይነግሥ በሐማት ምድር በምትገኘው በሪብላ እስረኛ በማድረግ፥ ይሁዳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ብር፥ ሠላሳ አራት ኪሎ ወርቅ ግብር እንዲከፍል ባደረገው ጊዜ የኢዮአካዝ ዘመነ መንግሥት ፍጻሜ ሆነ።
የግብጽም ንጉሥ ወንድሙን ኤልያቄምን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ፥ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው፤ ኒካዑም ወንድሙን ኢዮአክስን ይዞ ወደ ግብጽ ወሰደው።