ደግሞም የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመስደብ፥ በእርሱም ላይ ለመናገር፦ “የምድር አሕዛብ አማልክት ሕዝባቸውን ከእጄ ለማዳን እንዳልቻሉ፥ እንዲሁ የሕዝቅያስ አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ሊያድን አይችልም” የሚል ደብዳቤ ጻፈ።
2 ዜና መዋዕል 32:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቶቼ ካጠፉአቸው ከአሕዛብ አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄ ለማዳን የቻለ ማንስ ነበር፤ እናንተንስ አምላካችሁ ከእጄ ለማዳን የሚችል ይመስላችኋልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቶቼ ሙሉ በሙሉ ከደመሰሷቸው ከእነዚህ መንግሥታት አማልክት ሁሉ፣ ሕዝቡን ከእጄ ሊያድን የቻለ አምላክ የትኛው ነው? ታዲያ አምላካችሁ እንዴት ከእጄ ሊታደጋችሁ ይችላል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቶቼ ካወደሙአቸው ከእነዚህ አገሮች አማልክት መካከል አንዱ እንኳ አገሩን ያዳነበት ጊዜ አለን? ታዲያ፥ የእናንተ አምላክ ከእጄ እንዴት ሊያድናችሁ ይችላል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችሁስ ከእጄ እናንተን ለማዳን ይችል ዘንድ አባቶች ካጠፉአቸው ከአሕዛብ አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄ ያድን ዘንድ የቻለ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችሁስ ከእጄ እናንተን ለማዳን ይችል ዘንድ አባቶቼ ካጠፉአቸው ከአሕዛብ አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄ ያድን ዘንድ የቻለ ማን ነው? |
ደግሞም የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመስደብ፥ በእርሱም ላይ ለመናገር፦ “የምድር አሕዛብ አማልክት ሕዝባቸውን ከእጄ ለማዳን እንዳልቻሉ፥ እንዲሁ የሕዝቅያስ አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ሊያድን አይችልም” የሚል ደብዳቤ ጻፈ።