2 ዜና መዋዕል 29:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ መንግሥቱና ስለ መቅደሱም ስለ ይሁዳም ሰባት ወይፈኖች፥ ሰባትም አውራ በጎች፥ ሰባትም የበግ ጠቦቶች፥ ሰባትም አውራ ፍየሎች ለኃጢአት መሥዋዕት አመጡ። የአሮንንም ልጆች ካህናቱን፦ “በጌታ መሠዊያ ላይ አሳርጉአቸው” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ስለ መንግሥቱ፣ ስለ መቅደሱና ስለ ይሁዳ ሰባት ወይፈኖች፣ ሰባት አውራ በጎች፣ ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና ሰባት ተባዕት የፍየል ጠቦቶች ለኀጢአት መሥዋዕት አቀረቧቸው፤ ንጉሡም እነዚህን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ እንዲያቀርቡ የአሮንን ዘሮች ካህናቱን አዘዘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ለንጉሣዊው ቤተሰብና ለይሁዳ ሕዝብ የኃጢአት ስርየት፥ እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ መንጻት መሥዋዕት ሆነው ለእግዚአብሔር ይቀርቡ ዘንድ ሰባት ኰርማዎችን፥ ሰባት የበግ አውራዎችን፥ ሰባት የበግ ጠቦቶችንና ሰባት ፍየሎችን አመጡ፤ ንጉሡም የአሮን ዘሮች የሆኑትን ካህናት እንስሶቹን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ መሥዋዕት አድርገው እንዲያቀርቡ አዘዛቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ መንግሥቱና ስለ መቅደሱም፥ ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል ለኀጢአት መሥዋዕት ሰባት ወይፈኖች፥ ሰባትም አውራ በጎች፥ ሰባትም የበግ ጠቦቶች፥ ሰባትም አውራ ፍየሎች አመጡ። የአሮንንም ልጆች ካህናቱን፥ “ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ ውጡ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ መንግሥቱና ስለ መቅደሱም ስለ ይሁዳም ሰባት ወይፈኖች፥ ሰባትም አውራ በጎች፥ ሰባትም የበግ ጠቦቶች፥ ሰባትም አውራ ፍየሎች ለኃጢያት መሥዋዕት አመጡ። የአሮንንም ልጆች ካህናቱን “በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አሳርጉአቸው” አላቸው። |
ከእስር የመጡት ከምርኮ የተመለሱት ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ ስለ እስራኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት ወይፈኖች፥ ዘጠና ስድስት አውራ በጎች፥ ሰባ ሰባት ጠቦቶች፥ ለኃጢአት መሥዋዕት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎች አቀረቡ። ይህ ሁሉ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ።
አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፥ የሚቃጠልንም መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ አሳርጉ፥ አገልጋዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፥ እኔም እንደ ጥፋታችሁ እንዳላደርግባችሁ ጸሎቱን እሰማለሁ፥ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ቅን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና።”
በበዓሉም በሰባቱ ቀኖች የሚቃጠለውን መሥዋዕት በየዕለቱ ነውር የሌለባቸውን ሰባት ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች በሰባቱም ቀኖች ለጌታ ያቅርብ፤ ለኃጢአትም መሥዋዕት በየዕለቱ አንድ አውራ ፍየል ያቅርብ።
ወደ ጾፊምም ሜዳ ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ ላይ ወሰደው፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን አንድም አውራ በግ አሳረገ።