2 ዜና መዋዕል 27:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀረውም የኢዮአታም ነገር፥ ያደረገውም ጦርነት ሁሉ፥ ሥራውም፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢዮአታም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባር፣ ያደረጋቸው ጦርነቶችና አካሄዱ ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢዮአታም ዘመነ መንግሥት የተፈጸመው ሌላው ድርጊት ሁሉ፥ ያካሄደው ጦርነትና የመንግሥቱ አመራር ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጻሕፍት ተመዝግበው ይገኛሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀሩትም የኢዮአታም ነገሮች፥ ሰልፉም ሁሉ፥ ሥራውም፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረውም የኢዮአታም ነገር፥ ሰልፉም ሁሉ፥ ሥራውም፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል። |