2 ዜና መዋዕል 26:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዖዝያንም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ስድስት ዓመት ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ኀምሳ ሁለት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ይኮልያ የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዖዝያን በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ዐሥራ ስድስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ዐምሳ ሁለት ዓመት ገዛ። እናቱ ይኮልያ የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዖዝያ በዐሥራ ስድስት ዓመቱ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኀምሳ ሁለት ዓመት ገዛ፤ እናቱ ይኮልያ ተብላ የምትጠራ የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዖዝያንም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የዐሥራ ስድስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አምሳ ሁለት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ኢዮኮልያስ የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዖዝያንም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የዐሥራ ስድስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አምሳ ሁለት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ይኮልያ የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች። |
በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም፥ በአካዝና በሕዝቅያስም ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣው የጌታ ቃል ይህ ነው።
የአሞጽ ቃላት፥ በቴቁሔ ከሚገኙ ከበግ አርቢዎች መካከል የነበረ፥ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ የምድር መናወጥ ከመሆኑ ከሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል ያየው ይህ ነው።
የተራሮችም ሸለቆ እስከ አጸል ስለሚደርስ፥ በተራሮች መካከል ባለው ሸለቆ ትሸሻላችሁ። በይሁዳም ንጉሥ በዖዝያን ዘመን በምድር መንቀጥቀጥ ምክንያት ከሆነው ሽሽት በበለጠ ትሸሻላችሁ። ከዚያም አምላኬ ጌታ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል።