አብያም የተመረጡትን አራት መቶ ሺህ ኃያላን ተዋጊዎች ይዞ ወደ ጦርነት ወጣ፤ ኢዮርብዓምም የተመረጡትን ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ይዞ በእርሱ ላይ ተሰለፈ።
2 ዜና መዋዕል 26:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች የጽኑዓን ኃያላኑ ቍጥር ሁሉ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተዋጊዎቹ ላይ የተሾሙት የየቤተ ሰቡ መሪዎች ጠቅላላ ቍጥር ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሠራዊቱም የሚመራው በሁለት ሺህ ስድስት መቶ የጐሣ መሪዎች ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች በሰልፍ ጽኑዓንና ኀያላን የሆኑ ሁሉ ቍጥራቸው ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች የጽኑዓን ኃያላኑ ቍጥር ሁሉ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበር። |
አብያም የተመረጡትን አራት መቶ ሺህ ኃያላን ተዋጊዎች ይዞ ወደ ጦርነት ወጣ፤ ኢዮርብዓምም የተመረጡትን ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ይዞ በእርሱ ላይ ተሰለፈ።
ደግሞም ለዖዝያን በሠራዊቱ ውስጥ ለውግያ ብቁ የሆኑ ወታደሮች ነበሩት፤ በንጉሡ አለቃ በሐናንያ ትእዛዝ በአለቃው በመዕሤያና በጸሐፊው በይዒኤል እጅ እንደ ተቈጠሩ ወደ ሰልፍ በየቁጥራቸው ይወጡ ነበር።
ንጉሡንም በጠላቱ ላይ እንዲያግዝ፥ በታላቅ ኃይል ወደ ጦርነት የሚወጣ፥ በትእዛዛቸው ሥር የነበረ ሠራዊት ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ነበረ።