2 ዜና መዋዕል 24:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም አዘዘ፥ ሣጥንም ሠርተው በጌታ ቤት በር አጠገብ በስተ ውጭ አኖሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በንጉሡም ትእዛዝ የገንዘብ መሰብሰቢያ ሣጥን ሠርተው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መግቢያ በር አጠገብ በውጭ በኩል አኖሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ኢዮአስ “የገንዘብ መሰብሰቢያ ሣጥን ሠርታችሁ በቤተ መቅደሱ ቅጽር በር በስተውጭ በኩል አኑሩት” ሲል ሌዋውያኑን አዘዘ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ሣጥን ሠርተው በእግዚአብሔር ቤት በር አጠገብ በስተውጭ ያኖሩት ዘንድ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም አዘዘ፤ ሣጥንም ሠርተው በእግዚአብሔር ቤት በር አጠገብ በስተ ውጭ አኖሩት። |
ኢየሱስ በገንዘብ ማስቀመጫው አንጻር ተቀምጦ ብዙ ሰዎች ስጦታቸውን ወደ ቤተ መቅደሱ ገንዘብ ማስቀመጫ ሳጥን ሲያስገቡ ይመለከት ነበር። ብዙ ሀብታሞች ብዙ ገንዘብ አስገቡ፤