2 ዜና መዋዕል 23:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሦስቱም አንዱ በንጉሥ ቤት ሁኑ፤ እንዲሁም ከሦስቱ አንዱ በመካከለኛው በር ሁኑ፤ ሕዝቡም ሁሉ በጌታ ቤት አደባባይ ይሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሦስተኛው ቤተ መንግሥቱን፣ አንድ ሦስተኛው ‘የመሠረት ቅጽር በር’ የተባለውን ጠብቁ፤ የቀሩት ሰዎች በሙሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይ ይሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላው አንድ ሦስተኛ እጅ ቤተ መንግሥቱን ይጠብቅ፤ የመጨረሻው አንድ ሦስተኛ እጅ የመሠረት ቅጽር በር ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ ይጠብቅ፤ ሕዝቡም ሁሉ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ውስጥ ይሰብሰቡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሦስት አንድ እጅም በንጉሡ ቤት ሁኑ፤ ሌላውም ከሦስት አንድ እጅ በመካከለኛው በር ሁኑ፤ ሕዝቡም ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሦስት አንድ እጅም በንጉሥ ቤት ሁኑ፤ አንድ እጅም በመካከለኛው በር ሁኑ፤ ሕዝቡም ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ይሁኑ። |
ወደ ጌታ ቤት ግን ከካህናትና ከአገልጋዮቹ ሌዋውያን በቀር ማንም አይግባ፤ እነርሱ ቅዱሳን ናቸውና ይግቡ፤ ሕዝቡም ሁሉ ግን የጌታን ሕግ ይጠብቅ።
እንዲሁም አደረጉ፤ አሮንም እጁን ዘረጋ፥ በበትሩም የምድሩን ትቢያ መታ፥ በሰውና በእንስሳም ላይ ተናካሽ ትንኝ ሆነ፤ በግብጽ ምድር ያለ የምድር ትቢያ ሁሉ ተናካሽ ትንኝ ሆነ።
ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ፥ ሰዎች ተሸክመው መልካም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ በየቀኑ ያስቀምጡት የነበሩ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ።