2 ዜና መዋዕል 18:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚክያስም እንዲህ አለ፦ “በደህና የተመለስህ እንደሆነ ጌታ በእኔ አልተናረም።” ዳግመኛም እርሱ፦ “እናንተ ሕዝቦች ሆይ! ሁላችሁም ስሙኝ!” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚክያስም፣ “አንተ በደኅና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አልተናገረም ማለት ነው!” አለ፤ ቀጥሎም፣ “እናንተ ሰዎች ሁላችሁ ስሙኝ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚክያስም “አንተ ከዘመቻ በደኅና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አማካይነት አልተናገረም ማለት ነው!” አለው። ቀጥሎም ድምፁን ከፍ በማድረግ “በዚህ የምትገኙ ሁሉ እኔ የተናገርኩትን ሁሉ ልብ ብላችሁ አድምጡ!” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚክያስም፥ “በደኅና ብትመለስ እግዚአብሔር በእኔ አልተናገረም” አለ። “ደግሞም እናንተ ሕዝቡ ሁሉ ስሙኝ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚክያስም “በደህና ብትመለስ እግዚአብሔር በእኔ የተናገረ አይደለም” አለ። ደግሞም “እናንተ ሕዝብ ሁሉ፥ ስሙኝ” አለ። |