በገለዓድ ራሞት ቤን ጌቤር ተብላ የምትጠራው ከተማ፥ በገለዓድ የምናሴ ዘር የሆነው የያኢር ጐሣ ይዞታዎች የሆኑት መንደሮች፥ በባሳን አርጎብ ተብላ የምትጠራው ግዛት፥ እንዲሁም በሮቻቸው የነሐስ መወርወሪያ ባሉአቸው የቅጽር ግንቦች የተመሸጉ በድምሩ የስድሳ ታላላቅ መንደሮች አስተዳዳሪ።
2 ዜና መዋዕል 18:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነቢያትም ሁሉ፦ “ጌታ በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ወደ ሬማት ዘገለዓድ ሂድ፥ ለአንተም ይከናወንልሃል” እያሉ ተመሳሳይ የሆነን ትንቢት ይናገሩ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀሩትም ነቢያት ሁሉ፣ “እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና፣ በገለዓድ በምትገኘው ራሞት ላይ ዝመትባት” በማለት ተመሳሳይ ትንቢት ይናገሩ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎቹም ነቢያት ይህንኑ ቃል በመደገፍ “በራሞት ላይ ዝመት፤ ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔር ድልን ይሰጥሃል” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነቢያትም ሁሉ፥ “እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ወደ ሬማት ዘገለዓድ ውጣና ተከናወን” እያሉ እንዲሁ ትንቢት ይናገሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነቢያትም ሁሉ “እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ወደ ሬማት ዘገለዓድ ሂድና ተከናወን” እያሉ እንዲሁ ትንቢት ይናገሩ ነበር። |
በገለዓድ ራሞት ቤን ጌቤር ተብላ የምትጠራው ከተማ፥ በገለዓድ የምናሴ ዘር የሆነው የያኢር ጐሣ ይዞታዎች የሆኑት መንደሮች፥ በባሳን አርጎብ ተብላ የምትጠራው ግዛት፥ እንዲሁም በሮቻቸው የነሐስ መወርወሪያ ባሉአቸው የቅጽር ግንቦች የተመሸጉ በድምሩ የስድሳ ታላላቅ መንደሮች አስተዳዳሪ።
ሚክያስንም ሊጠራ የሄደ መልክተኛ ሚክያስን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ነቢያት በአንድ ድምፅ ሆነው ለንጉሡ መልካም ነገር ይናገራሉ፤ ቃልህም እንደ ቃላቸው እንዲሆን መልካም እንድትናገር እለምንሃለሁ።”
የእስራኤልም ንጉሥ አራት መቶ ነቢያትን ሰብስቦ፦ “ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለጦርነት እንሂድን? ወይስ ልቅር?” አላቸው። እነርሱም፦ “ጌታ በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ውጣ” አሉት።
አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛውም ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።