ኢዮሣፍጥም ከሌዋውያንና ከካህናት ከእስራኤልም የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ በጌታ ስም ፍርድን እንዲፈርዱ በሙግትም ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ በኢየሩሳሌም ሾመ። እነርሱም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።
2 ዜና መዋዕል 17:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም ጋር ሌዋውያንን ሸማያን፥ ነታንያን፥ ዝባድያን፥ አሣሄልን፥ ሰሚራሞትን፥ ዮናትንን፥ አዶንያስን፥ ጦብያን፥ ጦባዶንያን ላከ ከእነርሱም ጋር ካህናቱን ኤሊሳማንና ኢዮራምን አብሮ ላከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነዚህም ጋራ ጥቂት ሌዋውያን ነበሩ፤ ስማቸውም፦ ሸማያ፣ ነታንያ፣ ዝባድያ፣ አሣሄል፣ ሰሚራሞት፣ ዮናታን፣ አዶንያስ፣ ጦብያና ጦባዶንያ ነበር። ካህናቱ ደግሞ ኤሊሳማና ኢዮራም ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም ጋር ዘጠኝ ሌዋውያንና ሁለት ካህናት ነበሩ፤ ሌዋውያኑ ሸማዕያ፥ ነታንያ፥ ዘባድያ፥ ዐሣሄል፥ ሸሚራሞት፥ ይሖናታን፥ ኦዶኒያ፥ ጦቢያና ጦባዶኒያ ሲሆኑ ካህናቱ ደግሞ ኤሊሻማዕና ይሖራም ናቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም ጋር ሌዋውያንን ሸማያን፥ ነታንያን፥ ዛባድያን፥ አሣሄልን፥ ሰሚራሞትን፥ ዮናታንን፥ አዶንያስን፥ ጦብያን፥ ጦባዶንያስን ከእነርሱም ጋር ካህናቱን ኤሊሳማንና ኢዮራምን ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም ጋር ሌዋውያንን፥ ሸማያን፥ ነታንያን፥ ዝባድያን፥ አሣሄልን፥ ሰሚራሞትን፥ ዮናትንን፥ አዶንያስን፥ ጦብያንና ጦባዶንያን ሰደደ፤ ከእነርሱም ጋር ካህናቱን ኤሊሳማንና ኢዮራምን ሰደደ። |
ኢዮሣፍጥም ከሌዋውያንና ከካህናት ከእስራኤልም የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ በጌታ ስም ፍርድን እንዲፈርዱ በሙግትም ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ በኢየሩሳሌም ሾመ። እነርሱም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።
እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለጌታም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ “ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤ አሁንም አምላካችሁን ጌታንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ፤