1 ጢሞቴዎስ 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ከሃይማኖት ጋር ያለኝ ይበቃኛል ማለት ትልቅ ጥቅም የሚያስገኘ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እውነተኛ መንፈሳዊነት ባለን ነገር ከመርካት ጋራ ትልቅ ትርፍ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ያለኝ ይበቃኛል” ለሚል ሰው እግዚአብሔርን ማምለክ ትልቅ ጥቅም ያስገኝለታል። መንፈሳዊነትን ስለሚያተርፍበት ሃይማኖት የሀብት ምንጭ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ኑሮዬ ይበቃኛል፤” ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ |
ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፥ በክፉዎች ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት ደጃፍ ላይ መቅረትን መረጥሁ።
ወታደሮችም እንዲሁ፦ “እኛስ ምን እናድርግ?” ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም፦ “ማንንም በግፍ ወይም በሐሰት ክስ አትበዝብዙ፤ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ፤” አላቸው።
ሰውነትን አካላዊ እንቅስቃሴ ማለማመድ መጠነኛ ጠቀሜታ ቢኖረውም እንኳ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣውን ሕይወት የተስፋ ቃል ስላለው፥ ለሁሉ ነገር ይጠቅማል።