1 ጢሞቴዎስ 4:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ትእዛዝ ለወንድሞች ብታሳውቅ፥ በእምነትና በተከተልኸው በመልካም ትምህርት ቃላት እየተመገብክ ያደግህ፥ የክርስቶስ ኢየሱስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ትእዛዝ ለወንድሞች ብታሳስብ፣ በእምነት ቃልና በተቀበልኸው መልካም ትምህርት ታንጸህ የክርስቶስ ኢየሱስ በጎ አገልጋይ ትሆናለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ትምህርት ለአማኞች ብታስገነዝብ የእምነትን ቃልና የምትከተለውን መልካም ትምህርት እየተመገብክ ያደግኽ፥ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ወንድሞችን ብታሳስብ፥ በእምነትና በተከተልኸው በመልካም ትምህርት ቃል የምትመገብ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ወንድሞችን ብታሳስብ፥ በእምነትና በተከተልኸው በመልካም ትምህርት ቃል የምትመገብ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ። |
እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው፤’ እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።”
በዚህ ምክንያት የተወደደውንና የታመነውን በጌታ ልጄ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ፤ በየስፍራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እኔ እንደማስተምረው በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነው መንገዴን እርሱ ያሳስባችኋል።
እንደ እብድ ሰው እናገራለሁ፤ እኔ እበልጣቸዋለሁ፤ በሥራ ብዙ ደክሜአለሁ፥ ብዙ ጊዜ ታስሬለሁ፥ ብዙ ግርፋት ደርሶብኛል፥ ብዙ ጊዜ እስከ መሞት ደርሻለሁ።
እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ላልሆነ፥ ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን አበቃን፤ ፊደል ይገድላል፤ መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።
እናንተ ደግሞ በምን ሁኔታ እንዳለሁና እንዴት እንደምኖር እንድታውቁት የተወደደ ወንድምና በጌታ የታመነ አገልጋይ ቲኪቆስ ሁሉን ይነግራችኋል፤
እንዲሁም እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ የሚያድገውን አካል ሁሉ የሚንከባከበውን በመገጣጠምያዎቹና በጅማቶቹ አብሮ የሚያስተሳስረውን ራስ በጽኑ ሳይዝ ማንም አያውግዛችሁ።
የክርስቶስ ቃል በሙላት በእናንተ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩም፤ በመዝሙርና በውዳሴ በመንፈሳዊም ዝማሬ በልባችሁ በማመስገን ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤
ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን፥ የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው፤
ለሴሰኞች፥ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፥ በሰዎችም ለሚነግዱ፥ ለሐሰተኞችም፥ በውሸትም ለሚምሉና የእውነተኛ ትምህርት ተቃራኒ የሆነውን ነገር ሁሉ ለሚያደርጉ ነው።
ማንም ሰው ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከታመኑ ቃላት ጋራ የማይስማማና እግዚአብሔርን በመምሰል ላይ መሠረት ካደረገው ትምህርት ጋር የማይጣጣም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከሆነ፥
ሰዎች እውነተኛውን ትምህርት የማይታገሱበት፤ ይልቁንም ጆሮዎቻቸውን የሚኮረኩራቸውን ነገር በመሻት ለራሳቸው ምኞት የሚመቹ አስተማሪዎችን የሚሰበስቡበት ጊዜ ይመጣልና።
ነገር ግን ሁሉን ነገር አንድ ጊዜ ያወቃችሁትን እናንተን፥ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።