ከዚህ በኋላ ከቤትኤል የመጣው ሽማግሌ ነቢይ “እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከጌታ የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል” አለው፤ ነገር ግን ዋሽቶ ነበር።
1 ጢሞቴዎስ 4:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ትምህርት ኅሊናቸውን በጋለ ብረት በማቃጠል አደንዝዘው ውሸትን በሚናገሩ ግብዞች በኩል የሚሰጥ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ ያለው ትምህርት የሚመጣው ኅሊናቸው በጋለ ብረት የተጠበሰ ያህል ከደነዘዘባቸው ግብዝ ውሸተኞች ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም ዐይነቱ ትምህርት የሚመነጨው በግብዝነት፥ ሐሰትን ሲናገሩ በጋለ ብረት እንደ ተተኮሰ ያኽል ሆኖ የደነዘዘ ኅሊናቸው ከማይወቅሳቸው ሰዎች ነው። |
ከዚህ በኋላ ከቤትኤል የመጣው ሽማግሌ ነቢይ “እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከጌታ የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል” አለው፤ ነገር ግን ዋሽቶ ነበር።
ጌታም ‘እንዴት አድርገህ ልታሳስተው ትችላለህ?’ አለው። መንፈሱም ‘ሄጄ የአክዓብ ነቢያት ሁሉ ሐሰት እንዲናገሩ አደርጋለሁ’ ሲል መለሰለት፤ እግዚአብሔርም ‘እንግዲያውስ ሄደህ አሳስተው፤ ይከናወንልሃል አለው።’”
በኢየሩሳሌምም ነቢያት መካከል አስደንጋጭ ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁላቸውም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
እነሆ፥ ሐሰትን ትንቢት በሚያልሙ በሚናገሩም፥ በሐሰታቸውና በድፍረታቸውም ሕዝቤን በሚያስቱ በነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ፤ እኔም አልላክኋቸውም አላዘዝኋቸውምም፥ ለእነዚህም ሕዝብ በማናቸውም ነገር አይጠቅሙአቸውም፥ ይላል ጌታ።
እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የገዛ ሆዳቸውን እንጂ ጌታችንን ክርስቶስን አያገለግሉምና፤ በሚያሳምን ንግግርና በሽንገላ የየዋሆችን ልብ ያታልላሉ።
ከእንግዲህ እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል፥ በሰዎችም ማታለል ምክንያት፥ በነፈሰው የትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን፥ ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን፥ ሕፃናት መሆን አይገባንም።
የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ ምልክት እያደረጉ፥ በታላቁና ሁሉን በሚገዛው በእግዚአብሔር ቀን ለሚሆነው ጦርነት እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።