1 ተሰሎንቄ 4:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጸጥታ ለመኖር እንድትተጉ፥ በራሳችሁም ጉዳይ ላይ እንድታተኩሩ፥ እንዳዘዝናችሁም በራሳችሁ እጅ እንድትሰሩ እንለምናችኋለን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በፊት እንዳዘዝናችሁ በገዛ እጃችሁ ሥሩ፤ በጸጥታ ኑሩ፤ በራሳችሁ ጕዳይ ላይ ብቻ አተኵሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጸጥታም ለመኖር እንድትጣጣሩ እና የራሳችሁን ጉዳይ እንድታስቡ ከዚህ በፊት እንዳዘዝናችሁም በገዛ እጃችሁ እንድትሠሩ ነው። |
ይህም ቤቱን ለአገልጋዮቹ ትቶ፥ እያንዳንዱን አገልጋይ በየሥራ ድርሻው ላይ አሰማርቶ፥ በረኛው ነቅቶ እንዲጠብቅ አዝዞ የሄደውን ሰው ይመስላል።
እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው፤’ እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።”
እንዲሁም እግዚአብሔርን በመምሰልና በተገባ አካሄድ ሁሉ፥ ጸጥታ የሰፈነበትና ሰላማዊ የሆነ ሕይወት እንዲኖረን ስለ ነገሥታትና በከፍተኛ ሥልጣን ላይ ስላሉ ሁሉ ጸሎት እናቅርብ።
ከዚህም ጎን ለጎን ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ ፈቶችም ብቻ ሳይሆኑ የማይገባቸውን እየተናገሩ ሰውን የሚያሙና በነገር ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ።
ማንም ከእናንተ መካከል እንደ ነፍሰ ገዳይ፥ ወይም እንደ ሌባ፥ ወይም እንደ ክፉ አድራጊ፥ ወይም በሌሎች ጉዳይ ጣልቃ እንደሚገባ ሆኖ መከራ የሚቀበል አይኑር።