1 ተሰሎንቄ 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! በእምነታችሁ በኩል በችግራችንና በመከራችን ሁሉ ስለ እናንተ ተጽናናን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ በጭንቀታችንና በመከራችን ሁሉ በእምነታችሁ ምክንያት በእናንተ ተጽናናን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፥ እኛ የምንገኘው በችግርና በመከራ ውስጥ ቢሆንም እንኳ በእምነታችሁ ምክንያት በእናንተ ተጽናንተናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! በእምነታችሁ በኩል በችግራችንና በመከራችን ሁሉ ስለ እናንተ ተጽናናን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በእምነታችሁ በኩል በችግራችንና በመከራችን ሁሉ ስለ እናንተ ተጽናናን፤ |
አሁን ግን ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ወደ እኛ መጥቶ ስለ እምነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ መልካም ዜና አመጣልን፤ እኛ እናንተን ለማየት እንደምንናፍቅ እናንተም እኛን ለማየት እንደምትናፍቁና ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስታውሱን ደግሞ ነገረን፤