La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 9:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከማምለኪያው ኰረብታ ወደ ከተማዪቱ ከወረዱ በኋላ ሳሙኤል በቤቱ ሰገነት ላይ ከሳኦል ጋር ተነጋገረ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከማምለኪያው ኰረብታ ወደ ከተማዪቱ ከወረዱ በኋላ ሳሙኤል በቤቱ ሰገነት ላይ ከሳኦል ጋራ ተነጋገረ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከማምለኪያውም ስፍራ ወርደው ወደ ከተማይቱ በገቡ ጊዜ በሳሙኤል ቤት ሰገነት ላይ ለሳኦል አልጋ ተዘጋጀለት፤ እርሱም እዚያ ተኝቶ ዐደረ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከባማ ኮረ​ብ​ታም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ወረዱ፤ ሳሙ​ኤ​ልም ለሳ​ኦል በሰ​ገ​ነቱ ላይ መኝታ አዘ​ጋ​ጀ​ለት፤ እር​ሱም ተኛ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከኮረብታውም መስገጃ ወደ ከተማይቱ ወረዱ፥ ሳሙኤልም ለሳኦል በሰገነቱ ላይ መኝታ አዘጋጀለት፥ እርሱም ተኛ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 9:25
9 Referencias Cruzadas  

አንድ ቀን ማታ፥ ዳዊት ከአልጋው ተነሥቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፥ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ ውብ ነበረች።


ሕዝቡም ወጥተው አመጡ፥ እያንዳንዱ በቤቱ ሰገነት ላይ፥ በየግቢያቸው፥ በእግዚአብሔር ቤት ግቢ፥ በ “ውኃ በር” አደባባይና በኤፍሬም በር አደባባይ ላይ ዳሶችን ሠሩ።


የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች፥ እነዚያ በሰገነቶቻቸው ላይ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ ያጠኑባቸው፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቁርባን ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ፥ እንደ ቶፌት ስፍራ የረከሱ ይሆናሉ።’ ”


በጨለማ የነገርሁአችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮአችሁ የሰማችሁትን በሰገነት ላይ ስበኩ።


በጣራ ላይ ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፤


ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ እርሱን ለማስገባት ምንም ዓይነት መንገድ ባለማግኘታቸው ወደ ሰገነቱ ወጡ፤ የጣራውንም ጡብ አሳልፈው በመካከላቸው ከነአልጋው በኢየሱስ ፊት አወረዱት።


እነርሱም በነገው ሲሄዱ ወደ ከተማም ሲቀርቡ፥ ጴጥሮስ በስድስት ሰዓት ያህል ይጸልይ ዘንድ ወደ ሰገነት ወጣ።


“አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ፥ ከጣራው ላይ ሰው ወድቆ በቤትህ ላይ የደም በደል እንዳታመጣ፥ በጣራው ዙሪያ መከታ አብጅለት።


በነጋም ጊዜ በማለዳ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፥ “ላሰናብትህ ስለሆነ ተዘጋጅ” አለው። ሳኦልም ተዘጋጅቶ እንዳበቃ፥ ከሳሙኤል ጋር ተያይዘው ወደ ውጭ ወጡ።