La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 7:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፍልስጥኤማውያንም እስራኤል በምጽጳ መሰብሰባቸውን በሰሙ ጊዜ፥ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ሊወጓቸው ወጡ። እስራኤላውያንም ይህን ሲሰሙ ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እስራኤል በምጽጳ መሰብሰባቸውን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣ የፍልስጥኤማውያን ገዦች ሊወጓቸው ወጡ፤ እስራኤላውያንም ይህን ሲሰሙ፣ ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤላውያን በምጽጳ መሰብሰባቸውንም ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች አደጋ ሊጥሉባቸው ወጡ፤ እስራኤላውያንም ይህን በሰሙ ጊዜ ፈሩ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ተሰ​በ​ሰቡ በሰሙ ጊዜ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዘመቱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሰም​ተው ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ፈሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፍልስጥኤማውያንም የእስራኤል ልጆች ወደ ምጽጳ እንደ ተሰበሰቡ በሰሙ ጊዜ የፍልስጥኤማውያን አለቆች በእስራኤል ላይ ወጡ፥ የእስራኤልም ልጆች ሰምተው ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 7:7
4 Referencias Cruzadas  

ኢዮሣፍጥም ፈራ፥ ጌታንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ።


ፈርዖንም በቀረበ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ዓይናቸውን አነሡ፥ እነሆም ግብፃውያን ከኋላቸው እየመጡ ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች እጅግ ፈሩ፥ ወደ ጌታም ጮኹ።


እስራኤላውያን ያሉበት ሁኔታ እጅግ አስጊ መሆኑንና ሠራዊታቸውም በከባድ ጭንቀት ውስጥ መግባቱን ባዩ ጊዜ፥ በየዋሻውና በየቁጥቋጦው፥ በየዐለቱ መካከልና በየገደሉ እንዲሁም በየጉድጓዱ ሁሉ ተሸሸጉ።


ሳኦልና እስራኤላውያን ሁሉ የፍልስጥኤማዊውን ቃል በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ ደነገጡም።