La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 3:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ እፈጽማለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በዔሊና በቤተ ሰቡ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ እፈጽማለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ አስቀድሜ የተናገርኩትን ብርቱ የማስጠንቀቂያ ቃል ሁሉ በተግባር እፈጽማለሁ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም ቀን በቤቱ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሁሉ በዔሊ ላይ አጸ​ና​ለሁ፤ እኔም ጀምሬ እፈ​ጽ​ም​በ​ታ​ለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያም ቀን በቤቱ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ በዔሊ አወርዳለሁ፥ እኔም ጀምሬ እፈጽምበታለሁ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 3:12
11 Referencias Cruzadas  

እኔ ጌታ ሰይፌን ከሰገባው እንደ መዘዝሁ ሥጋ ለባሽ ሁሉ ያውቃል፤ እርሱም ደግሞ ወደ ሰገባው አይመለስም።


ነገር ግን ለአገልጋዮቼ ለነቢያት ያዘዝኳቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? ከዚያ እነርሱም ተጸጽተው፦ “የሠራዊት ጌታ በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ሊያደርግብን ያሰበውን እንዲሁ አድርጎብናል” በማለት ተቀበሉ።


ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?


ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።


ጌታ አምላካችሁ የተናገረው መልካም ነገር ሁሉ እንደ ተከናወነላችሁ፥ ጌታ አምላካችሁ ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እናንተን እስኪያጠፋችሁ ድረስ ጌታ እንዲሁ ክፉን ነገር ሁሉ ያመጣባችኋል።


ከነዓናዊውን ንጉሥ ኢያቢስን እስኪደመስሱ ድረስ የእስራኤላውያን ክንድ እየበረታ ሄደ።


የእግዚአብሔር ታቦት ተማረከ፤ ሁለቱም የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስ ተገደሉ።


ወሬውን ያመጣውም ሰው፥ “እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ሠራዊቱም ከፍተኛ እልቂት ደርሶበታል፤ እንዲሁም ሁለቱ ልጆችህ ሖፍኒና ፊንሐስ ሞተዋል፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት ተማርኳል” ብሎ መለሰለት።


የእግዚአብሔር ታቦት ስለ ተማረከ፥ ዐማቷና ባሏም ስለ ሞቱ፥ “ክብር ከእስራኤል ተለይቷአል” ስትል የሕፃኑን ስም ኢካቦድ አለችው።


ከዚያም፥ “የእግዚአብሔር ታቦት ተማርኳልና ክብር ከእስራኤል ተለይቶአል” አለች።