1 ሳሙኤል 26:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “አንተ ብርቱ ሰው አይደለህምን? በእስራኤልስ ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? እነሆ፤ አንድ ሰው ንጉሡን ጌታህን ለመግደል መጥቶ ነበር፤ ታዲያ አንተ ንጉሥ ጌታህን ያልጠበቅኸው ስለ ምንድነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም ለአበኔር እንዲህ አለ፤ “አንተ ብርቱ ሰው ነህ? በእስራኤልስ ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? እነሆ፤ አንድ ሰው ንጉሡን ጌታህን ለመግደል መጥቶ ነበር፤ ታዲያ አንተ ንጉሥ ጌታህን ያልጠበቅኸው ስለ ምንድን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም “አበኔር! አንተ በእስራኤል የታወቅህ ታላቅ ሰው አይደለህምን? ታዲያ ጌታህን ንጉሡን በደንብ የማትጠብቀው ስለምንድን ነው? እነሆ፥ ከእኛ አንድ ሰው ጌታህን ለመግደል ወደ ሰፈር ገብቶ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም አቤኔርን፥ “አንተ ጐልማሳ አይደለህምን? በእስራኤል ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? ጌታህን ንጉሡን ለመግደል አንድ ሰው ገብቶ ነበርና ጌታህን ንጉሡን የማትጠብቅ ስለምን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም አበኔርን፦ አንተ ጕልማሳ አይደለህምን? በእስራኤል ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? ጌታህን ንጉሡን ለመግደል አንድ ሰው ገብቶ ነበርና ጌታህን ንጉሡን የማትጠብቅ ስለ ምን ነው? |
ዳዊት ሠራዊቱንና የኔርን ልጅ አቤኔርን፥ “አቤኔር ሆይ፥ አትመልስልኝምን?” ሲል ተጣራ። አቤኔርም፥ “በንጉሡ ላይ የምትጮኽ አንተ ማነህ?” በማለት መለሰ።
ይህ ያደረግኸው ነገር መልካም አይደለም፤ በሕያው ጌታ ስም እምላለሁ፥ አንተና ሰዎችህ ሞት ይገባችኋል፤ ጌታ የቀባውን ጌታችሁን አልጠበቃችሁም። እስቲ ተመልከት፤ በራስጌው የነበሩት የንጉሡ ጦርና የውሃ መያዣ የት አሉ?”