La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 25:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታዬ፥ ያን ባለጌ ሰው ናባልን ከቁምነገር አይቁጠረው፤ ስሙ ራሱ ሞኝ ማለት ስለሆነ፥ ሰውየውም ልክ እንደ ስሙ ነው፤ ሞኝነትም አብሮት የኖረ ነው። እኔ አገልጋይህ ግን ጌታዬ የላካቸውን ጐልማሶች አላየኋቸውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጌታዬ፣ ያን ምናምንቴ ሰው ናባልን ከቁም ነገር አይቍጠረው፤ ስሙ ራሱ ሞኝ ማለት ስለ ሆነ፣ ሰውየውም ልክ እንደ ስሙ ነው፤ ሞኝነትም ዐብሮት የኖረ ነው። እኔ አገልጋይህ ግን ጌታዬ የላካቸውን ጕልማሶች አላየኋቸውም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የናባልን ጉዳይ ከቁም ነገር አታግባው! እርሱ ልክ እንድ አስሙ አጠራር ሞኝ ነው! ጌታዬ፥ የአንተ አገልጋዮች በመጡ ጊዜ እኔ በዚያ አልነበርኩም፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚህ ክፉ ሰው በና​ባል ላይ ጌታዬ ልቡን እን​ዳ​ይ​ጥል እለ​ም​ና​ለሁ፤ እንደ ስሙ እን​ዲሁ እርሱ ነው፤ ስሙ ናባል ነው፤ ስን​ፍ​ናም አድ​ሮ​በ​ታል፤ እኔ ባሪ​ያህ ግን አንተ የላ​ክ​ሃ​ቸ​ውን ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህን አላ​የ​ሁም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚህ ምናምንቴ ሰው በናባል ላይ ጌታዬ ልቡን እንዳይጣል እለምናለሁ፥ እንደ ስሙ እንዲሁ እርሱ ነው፥ ስሙ ናባል ነው፥ ስንፍናም አድሮበታል፥ እኔ ባሪያህ ግን ከአንተ የተላኩትን የጌታዬን ጕልማሶች አላየሁም።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 25:25
9 Referencias Cruzadas  

አሁንም የሞተው አምኖን ብቻ ስለሆነ፥ የንጉሡ ልጆች በሙሉ እንደተገደሉ አድርጎ ንጉሥ ጌታዬ በልቡ ማሰብ የለበትም።”


ጻድቅ የድሆችን መብት ይመለከታል፥ ክፉ ሰው ግን ይህንን አያስተውልም።


ከእንግዲህ ወዲህ ሰነፍ ጨዋ ተብሎ አይጠራም፤ ሸንጋይ ሰው የተከበረ አይባልም።


ስለዚህ የቁጣውን መዓትና የሰልፉን ጽናት አፈሰሰባቸው፤ በዙሪያቸውም አነደደው፤ እነርሱ ግን አላወቁም፥ አቃጠላቸውም እነርሱ ግን ልብ አላሉም።


“ባትሰሙ፥ ለስሜም ክብር ለመስጠት በልባችሁ ባታኖሩት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “እርግማን እልክባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማለሁ፤ አሁንም ረግሜዋለሁ ምክንያቱም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና።”


አሁንም በጌታችንና በመላው ቤተሰቡ ላይ መከራ እያንዣበበ ስለሆነ፥ ምን እንደምታደርጊ አስቢበት፤ እርሱ እንደሆነ እንዲህ ያለ ባለጌ ሰው ስለሆነ፥ ማንም ደፍሮ የሚነግረው የለም።”


በእግሩም ላይ ወድቃ እንዲህ አለች፤ “ጌታዬ ሆይ፤ በደሉ በእኔ ላይ ብቻ ይሁን፤ እባክህ አገልጋይህ ታናግርህ፤ የምትልህንም ስማ።


ጌታዬ ሆይ፤ በሕያው ጌታ፥ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ ደም ከማፍሰስና በገዛ እጅህ ከመበቀል የጠበቀህ ጌታ ነው፤ አሁንም ጠላቶችህና ጌታዬን ሊጐዱ የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ፤


የሰውየው ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢጌል ነበረ። እርሷም አስተዋይና ውብ ነበረች፤ ባሏ ግን ባለጌና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበረ፤ እርሱም ከካሌብ ወገን ነበር።