La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 23:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ሳኦል ዳዊትን ማሳደዱን ትቶ፥ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሊዋጋ ሄደ። ከዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም “የመለያያ ዓለት” ብለው ጠሩት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ሳኦል ዳዊትን ማሳደዱን ትቶ፣ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ሊዋጋ ሄደ። ከዚህ የተነሣም የዚያን ቦታ ስም ሐማለኮዝ ብለው ጠሩት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም ሳኦል ዳዊትን የማሳደድ ተግባሩን አቁሞ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ሄደ፤ ያም ቦታ “የማምለጥ አለት” ተብሎ የተጠራበት ምክንያት ይኸው ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ማሳ​ደ​ድን ትቶ ተመ​ለሰ። ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ሊዋጋ ሄደ። ስለ​ዚህ የዚያ ስፍራ ስም የመ​ለ​ያ​የት ዓለት ተባለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሳኦልም ዳዊትን ማሳደድ ትቶ ተመለስ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ሊዋጋ ሄደ። ስለዚህ የዚህ ስፍራ ስም የማምለጥ ዓለት ተባለ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 23:28
6 Referencias Cruzadas  

ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች፥ ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን።


ሳኦልና ሰዎቹም ዳዊትን ሊፈልጉት ሄዱ፤ እርሱም ይህን በሰማ ጊዜ፥ ወደ ዐለቱ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ተቀመጠ። ሳኦልም ይህን እንደሰማ፥ ዳዊትን በማሳደድ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ዘልቆ ገባ።


አንድ መልእክተኛ ወደ ሳኦል መጥቶ፥ “ፍልስጥኤማውያን አገሩን ወረውታልና ቶሎ ድረስ!” አለው።


ዳዊትም ከዚያ ወደ ላይ ወጥቶ በዔንገዲ ምሽጎች ተቀመጠ።


ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ከተመለሰ በኋላ፥ “እነሆ፥ ዳዊት በዔንገዲ ምድረ በዳ አለ” ብለው ነገሩት።