La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 18:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ከገደለ በኋላ፥ ሰዎቹ ወደየቤታቸው በሚመለሱበት ጊዜ፥ ሴቶች ከበሮና መሰንቆ ይዘው እየዘፈኑ፥ እየጨፈሩና እልል እያሉ ንጉሥ ሳኦልን ለመቀበል ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ከገደለ በኋላ፣ ሰዎቹ ወደ የቤታቸው በሚመለሱበት ጊዜ፣ ሴቶች ከበሮና መሰንቆ ይዘው እየዘፈኑ፣ እየጨፈሩና እልል እያሉ ንጉሥ ሳኦልን ለመቀበል ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊት ጎልያድን ገድሎ ሲመለስና ወታደሮችም ወደየቤታቸው በማምራት ላይ ሳሉ፥ በእስራኤል በሚገኙት ከተሞች ሁሉ የሚኖሩ ሴቶች ሳኦልን ለመቀበል ወጡ፤ እነርሱም በእልልታ እየዘፈኑና እየጨፈሩ፥ የመስንቆ ድምፅ እያሰሙ አታሞ ይመቱ ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ገድሎ በተ​መ​ለሰ ጊዜ፥ እየ​ዘ​መ​ሩና እየ​ዘ​ፈኑ፥ እል​ልም እያሉ ከበ​ሮና አታሞ ይዘው ዳዊ​ትን ሊቀ​በሉ ሴቶች ከእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞች ሁሉ ወጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲህም ሆነ፥ ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ፥ እየዘመሩና እየዘፈኑ እልልም እያሉ ከበሮና አታሞ ይዘው ንጉሡን ሳኦልን ሊቀበሉ ሴቶች ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 18:6
11 Referencias Cruzadas  

የፍልስጥኤም ቆነጃጅት ደስ እንዳይላቸው፤ ያልተገረዙት ሴት ልጆች እልል እንዳይሉ፤ ይህን በጌት አትናገሩ፤ በአስቀሎናም መንገዶች አታውጁ፤


ዳዊትና የእስራኤል ቤት በሙሉ በዝማሬ፥ በበገና፥ በመሰንቆ፥ በከበሮ፥ በጽናጽልና በቃጭል ድምፅ በጌታ ፊት ያሸበሽቡ ነበር።


ስሙን በሽብሸባ ያወድሱ፥ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት።


እንስሶችህ በውስጡ አደሩ፥ አቤቱ፥ በቸርነትህ ለድሆች አዘጋጀህ።


አምላክ ሆይ ጉዞህን አዩት፥ የአምላኬና የንጉሤ ንግደት ወደ ቤተ መቅደስ።


የአሮን እኅት ነቢይቱ ማሪያምም ከበሮ በእጅዋ ወሰደች፤ ሴቶችም ሁሉ ከበሮ በመያዝና በጭፈራ በኋላዋ ወጡ።


ማርያምም፦ “ለጌታ ዘምሩ በክብር ከፍ ከፍ ብሏልና፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ” እያለች ዘመረችላቸው።


ጌታ በላዩ የሚወርድበት የታዘዘበት የበትር ድብደባ ሁሉ በከበሮና በመሰንቆ የታጀበ ይሆናል፤ በጦርነትም ክንዱን አንሥቶ ይዋጋቸዋል።


ዮፍታሔ ምጽጳ ወዳለው ቤቱ ተመለሰ፤ እነሆ፤ ልጁ አታሞ እየደለቀች በመዝፈን ልትቀበለው ወጣች፤ እርሷም አንዲት ልጁ ብቻ ነበረች፤ ከእርሷ በቀር ወንድም ሆነ ሴት ልጅ አልነበረውም።


ሳኦል በሚልከው በማናቸውም ስፍራ፥ ዳዊት ተልእኮውን በሚገባ ይፈጽም ስለ ነበር፥ በሠራዊቱ ላይ ሾመው፤ ይህም ሕዝቡን በሙሉ፥ የሳኦልንም የጦር ሹማምንት ደስ አሰኘ።