እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ሆኖ ሥራውን ሁሉ ያሳካለት ስለ ነበር፥ የወህኒ ቤት አዛዡ በዮሴፍ ኀላፊነት ሥር ስላለው ስለማንኛውም ጉዳይ ሐሳብ አይገባውም ነበር።
1 ሳሙኤል 18:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል በሚልከው በማናቸውም ስፍራ፥ ዳዊት ተልእኮውን በሚገባ ይፈጽም ስለ ነበር፥ በሠራዊቱ ላይ ሾመው፤ ይህም ሕዝቡን በሙሉ፥ የሳኦልንም የጦር ሹማምንት ደስ አሰኘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል በሚልከው በማናቸውም ስፍራ፣ ዳዊት ተልእኮውን በሚገባ ይፈጽም ስለ ነበር፣ በሰራዊቱ ላይ ሾመው፤ ይህም ሕዝቡን በሙሉ፣ የሳኦልንም የጦር ሹማምት ደስ አሠኘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል በትእዛዝ በሚያዘምትበት ቦታ ሁሉ የዳዊት ተልእኮ የተሳካ ሆነ፤ ስለዚህም ሳኦል በጦር ሠራዊቱ ውስጥ የመኰንንነት ማዕርግ እንዲኖረው አደረገ፤ ይህም የሳኦልን የጦር መኰንኖችና ወታደሮችን ሁሉ አስደሰተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ሳኦል ወደ ላከው ሁሉ ይሄድ ነበር፤ አስተውሎም ያደርግ ነበር፤ ሳኦልም በጦረኞች ላይ ሾመው፤ ይህም በሕዝብ ሁሉ ዐይንና በሳኦል ባሪያዎች ዐይን መልካም ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ሳኦል ወደ ሰደደው ሁሉ ይሄድ ነበር፥ አስተውሎም ያደርግ ነበር፥ ሳኦልም በጦረኞች ላይ ሾመው፥ ይህም በሕዝብ ሁሉ ዓይንና በሳኦል ባሪያዎች ዓይን መልካም ነበረ። |
እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ሆኖ ሥራውን ሁሉ ያሳካለት ስለ ነበር፥ የወህኒ ቤት አዛዡ በዮሴፍ ኀላፊነት ሥር ስላለው ስለማንኛውም ጉዳይ ሐሳብ አይገባውም ነበር።
እንደ ትላንትና እንዳለፉት ሦስት ቀናት ሳኦል በእኛ ላይ ነግሦ በነበረ ጊዜ፥ እስራኤልን በጦርነት የምትመራቸው አንተ ነበርህ፤ ጌታም፥ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ መሪያቸውም ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”
እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለ፥ ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ፥ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፥ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
ጌታ ከይሁዳ ሰዎች ጋር ነበር፤ ስለዚህ ኰረብታማውን አገር ያዙ፤ ነገር ግን በረባዳማው ምድር የሚኖሩት ሰዎች ከብረት የተሠሩ ሠረገሎች ስለ ነበሯቸው ከዚያ አሳደው ሊያስወጧቸው አልቻሉም።
ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎች ከእስራኤል መረጠ፤ ሁለቱ ሺህ በማክማስና በተራራማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋር፥ አንዱ ሺህ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ ድንኳኖቻቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።
የፍልስጥኤማውያን ጦር አዛዦች እንደ ወትሮው ሁሉ ለጦርነት ይወጡ ነበር፤ ዳዊትም ከቀሩት የሳኦል መኳንንት የበለጠ ድል አገኘ፤ ስሙም እጅግ የታወቀ ሆነ።
ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ከገደለ በኋላ፥ ሰዎቹ ወደየቤታቸው በሚመለሱበት ጊዜ፥ ሴቶች ከበሮና መሰንቆ ይዘው እየዘፈኑ፥ እየጨፈሩና እልል እያሉ ንጉሥ ሳኦልን ለመቀበል ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ።