La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 14:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮናታንም እንዲህ አለ፤ “አባቴ በምድሪቱ ላይ ችግር ፈጥሯል፤ ከዚህ ማር ጥቂት በቀመስሁ ጊዜ ዐይኔ እንዴት እንደ በራ ተመልከቱ!

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዮናታንም እንዲህ አለ፤ “አባቴ በምድሪቱ ላይ ችግር ፈጥሯል፤ ከዚህ ማር ጥቂት በቀመስሁ ጊዜ ዐይኔ እንዴት እንደ በራ ተመልከቱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዮናታንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አባቴ በሕዝባችን ላይ የፈጠረው ችግር ምን ያኽል ከባድ ነው! ትንሽ ማር. አግኝቼ በመብላት ብርታት አግኝቼ ዐይኔ እንደ በራ ተመልከት!

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዮና​ታ​ንም “አባቴ ምድ​ሪ​ቱን አስ​ቸ​ገረ፤ ከዚህ ማር ጥቂት ብቀ​ምስ ዐይኔ እንደ በራ እዩ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮናታንም፦ አባቴ ምድሪቱን አስቸገረ፥ ከዚህ ማር ጥቂት ብቀምስ ዓይኔ እንደ በራ እዩ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 14:29
5 Referencias Cruzadas  

ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም!


እስከ መቼ በነፍሴ እጨነቃለሁ? ትካዜስ እስከ መቼ ዕለቱን በሙሉ በልቤ ይሆናል? እስከ መቼ ጠላቴ በላዬ ይሸልላል?


ኢያሱም፦ “ለምን መከራን አመጣህብን? ጌታ ዛሬ መከራን ያመጣብሃል” አለው፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሉአቸው፥ በድንጋይም ወገሩአቸው።


ከሕዝቡም አንድ ሰው፥ “አባትህ ሕዝቡን፥ ‘ዛሬ እህል የሚቀምስ ማናቸውም ሰው የተረገመ ይሁን!’ በማለት በጽኑ መሓላ አስጠንቅቆናል” አለው። ሰው ሁሉ ተዳክሞ ነበር።


ሕዝቡ ከጠላቶቻቸው እጅ ከወሰዱት ምርኮ ዛሬ በልተው ቢሆን ኖሮ ምንኛ በተሻለ ነበር፤ የተገደሉትም ፍልስጥኤማውያን ቍጥር ከዚህ በበለጠ ነበር።”