La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 12:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የምትፈሩና የምታመልኩ፥ የምትታዘዙትና በትእዛዛቱ ላይ የማታምጹ ከሆነ፥ እንዲሁም እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁን ጌታን ከተከተላችሁ፥ መልካም ይሆንላችኋል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርን የምትፈሩና የምታመልኩ፣ የምትታዘዙትና በትእዛዞቹ ላይ የማታምፁ ከሆነ፣ እንዲሁም እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ከተከተላችሁ መልካም ይሆንላችኋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርን ብትፈሩና ብታመልኩት፥ ቃሉንም ብታዳምጡ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ብትጠብቁ፥ እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ብትከተሉ ሁሉ ነገር ይሠምርላችኋል፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ብት​ፈሩ፥ ብታ​መ​ል​ኩ​ትም፥ ቃሉ​ንም ብት​ሰሙ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ላይ ባታ​ምፁ፥ እና​ን​ተና በእ​ና​ንተ ላይ የነ​ገ​ሠው ንጉሥ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ብት​ከ​ተሉ፥ መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርን ብትፈሩ ብታመልኩትም፥ ቃሉንም ብትሰሙ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ባታምፁ፥ እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ብትከተሉ፥ መልካም ይሆንላችኋል።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 12:14
11 Referencias Cruzadas  

አሳንም ሊያገኘው ወጣ፥ እንዲህም አለው፦ “አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ! ስሙኝ፤ እናንተ ከጌታ ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተውት ግን ይተዋችኋል።


ጨለማን ላከ፥ ጨለመባቸውም፥ በቃሉም ዐመፁ።


ጻድቃን መልካም ነገር እንደሚያገኙ ንገሯቸው፤ የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና። የእጃቸውን ያገኛሉና።


ጻዴ። በአፉ ነገር ላይ ዓመጽ አድርጌአለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ አሕዛብ ሁሉ፥ እባካችሁ፥ ስሙ መከራዬንም ተመልከቱ፥ ደናግሎቼና ጐበዛዝቴ ተማርከው ሄዱ።


በመልካም ሥራ በመጽናት ምስጋናንና ክብርን የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ የዘለዓለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል፤


ከግብጽ ባወጣችሁና ከባርነት ምድር በዋጃችሁ በአምላካችሁ በጌታ ላይ ሊያስታችሁ ተናግሮአልና፥ አምላካችሁ ጌታ እንድትከተሉት ካዘዛችሁ መንገድ እንድትመለሱ አድርጎአልና፥ ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ ስለዚህ ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ።”


“እንግዲህ አሁን ጌታን ፍሩ፥ በፍጹም ቅንነትና ታማኝነት አገልግሉት፤ አባቶቻችሁም በወንዝ ማዶ በግብጽም ውስጥ ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፥ ጌታንም አምልኩ።


ጌታን ትታችሁ እንግዶችን አማልክት ብታመልኩ፥ መልካም ካደረገላችሁ በኋላ ተመልሶ ክፉ ነገር ያደርግባችኋል፥ ያጠፋችኋልም።”