La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ጴጥሮስ 3:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሚሳቡትም አክብሮት የተሞላውንና ንጹሕ ኑሮአችሁን ሲመለከቱ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህም የሚሆነው ንጹሕና ፍጹም አክብሮት የተሞላውን ኑሯችሁን ሲመለከቱ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሊሳቡ የሚችሉትም ንጹሕ የሆነውንና ሰው አክባሪ የሆነውን ሕይወታችሁን ሲመለከቱ ነው።

Ver Capítulo



1 ጴጥሮስ 3:2
13 Referencias Cruzadas  

ሆኖም ከእናንተ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፤ ሚስትም ባልዋን ታክብር።


አገልጋዮች ሆይ! ለክርስቶስ እንደምትታዘዙ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ፥ በልባችሁ ቅንነት በምድር ጌቶቻችሁ ለሆኑ ታዘዙ፤


ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ብቻ ኑሩ፤ በዚህም መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል እምነት አብራችሁ መጋደላችሁንና በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁን እሰማለሁ።


እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፤ ከዚያም የሚመጣውን አዳኝ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤


ባርያዎች ሆይ! ሰውን ደስ ለማሰኘት ስትሉ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ፤ ነገር ግን በቅን ልብ ጌታን እየፈራችሁ ለምድራዊ ጌቶቻችሁ በሁሉ ታዘዙ።


ማንም ወጣትነትህን አይናቀው፤ ይልቅስ በንግግር፥ በኑሮ፥ በፍቅር፥ በእምነት፥ በንጽሕና፥ ለሚያምኑት ምሳሌ ሁን።


ነገር ግን የጠራችሁ እርሱ ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።


ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር በሚጎበኝበት ቀን፥ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ እርሱን እንድያከብሩት በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።


እንዲሁም እናንተ ሚስቶች ሆይ! ለባሎቻችሁ ታዘዙ፤ በዚህ ዓይነት አንዳንዶች በቃሉ የማያምኑ ቢሆኑም እንኳ ያለ ቃል በሚስቶቻቸው ጠባይ ብቻ ሊሳቡ ይችሉ ይሆናል።


ለእናንተም ቢሆን ውበታችሁ ውጫዊ የሆነ፥ ሹሩባ በመሠራት፥ በወርቅ በማጌጥና የከበረ ልብስ በመልበስ አይሁን፤


እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በዚህ ሁኔታ የሚጠፉ ከሆነ፥ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል መኖር አይገባችሁም?