በብልኀነታቸውና በጥንካሬአቸው ይህን አገር እንዴት አድርገው እንደያዙት አወሩለት፤ በእውነቱ ቦታው ከእነርሱ በጣም ሩቅ ነበር፤ እነርሱን ለመውጋት ከምድር ዳርቻ የመጡ ነገሥታትም ነበሩ፤ ብዙ ጉዳት አድርሰውባቸው አጥፋተዋቸዋል፤ ሌሎቹ ግን የዓመት ግብር ይከፍሏቸው ነበር፤