Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa 1ኛ መጽሐፈ መቃብያን 8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)የሮማውያን የምስጋና ቃል 1 የሮማውያን ዝና ወደ ይሁዳ ጆሮ ደረሰ፤ እነርሱ ጐበዝ ጦረኞች ነበሩ፤ ከጐናቸው ለማሰለፉ ሰዎች ሁሉ ደጐች ነበሩ፤ ወደ እነርሱ ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ ወዳጅነታቸውን የሚሰጡ (የሚለግሡ) ነበሩ፤ ጀግና ጦረኞች ነበሩ። 2 ያደረጓቸውን ዘመቻዎች፥ በገላትያ አገር የፈጸሟቸውን ብዝበዛዎች፥ የገላትያን ሰዎች ማሸነፋቸውንና እንዲገብሩ ማድረጋቸውን ለይሁዳ አወሩለት፤ 3 እዚያ የሚገኙትን የብርና የወርቅ ማዕድኖችን ለመውሰድ በእስጳንያ አገር ያደረጉትን እና 4 በብልኀነታቸውና በጥንካሬአቸው ይህን አገር እንዴት አድርገው እንደያዙት አወሩለት፤ በእውነቱ ቦታው ከእነርሱ በጣም ሩቅ ነበር፤ እነርሱን ለመውጋት ከምድር ዳርቻ የመጡ ነገሥታትም ነበሩ፤ ብዙ ጉዳት አድርሰውባቸው አጥፋተዋቸዋል፤ ሌሎቹ ግን የዓመት ግብር ይከፍሏቸው ነበር፤ 5 በመጨረሻም የኪቲማውያንን ንጉሥ ፊሊጶስን ጴርሰስንም በእነርሱ ላይ የተነሡባቸውን ሁሉ ወግተው አሸንፈዋቸዋል። 6 መቶ ሃያ ዝሆኖች፥ ፈረሰኛው ጦረኞችና የሠረገላ ጦረኞች እንዲሁም ብዙ ሠራዊት አስከትቶ ሊወጋቸው የመጣባቸውን የእስያ ንጉሥ የነበረውን አንጥዮኩስን አሸንፈውታል፤ 7 ንጉሡም በሕይወቱ ተይዞ እርሱም ወራሾቹም ከእርሱ በኋላ በተወሰነው ጊዜ ከባድ ግብር እንዲከፍሉ ተደርጐባቸዋል፤ ዋስም እንዲቀርብ ተደርጓል፤ 8 የሕንድ፥ የምድያም፥ የልድያ አገሮች እንዲሁም አንዳንድ ምርጥ አገሮች ተወስደውበት ለንጉሥ ዩሚነስ ተሰጥተውበታል። 9 የግሪክ ሰዎች ሄደው ሊፈጁዋቸው ፈልገው ነበር፤ 10 ሮማውን ነገሩን ባወቁ ጊዜ አንድ የጦር መሪ ብቻ ልከው ጦርነት ገጠሟቸው፤ ከግሪካውያን ብዙዎች ሞቱ፤ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው በውርስ ተወሰዱ፤ ሮማውያን ንብረታቸውን ዘርፈው ወሰዱባቸው፤ አገራቸውን አስገበሩ፤ ምሽጐቻቸውን አፈረሱ፤ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲያገለግሏቸው አድርገዋቸዋል። 11 እንዲሁም የተቃወሟቸውን መንግሥታትና ደሴቶች ደምስሰው አስገብረዋቸዋል። 12 ነገር ግን ወዳጆቻቸውንና በእነርሱ የሚተማመኑትን በተመለከተ ግን የገቡትን ቃል አያጥፉም። ሩቆችንም ሆነ ቅርቦችን ነገሥታት ይዘው አረብረዋል፤ ስማቸውን የሚሰሙ ሁሉ ይፈሩዋቸዋል። 13 መንገሥና እርዳታም ማግኘት ይገባቸዋል የሚሏቸውን ያነግሣሉ፥ ሌሎችን ግን ይሽራሉ፤ በጣም ከፍ ያለ ኃይል ያላቸው ናቸው። 14 ታዲያ ይህ ሁሉ ሲሆን አንድ እንኳ ከእነርሱ ዘውድ የደፋና ለመመካት ከፈይ የለበሰ የለም። 15 መልካም ሥርዓት እንዲጠበቅ የሕዝብን ጉዳዮች ሁልጊዜ የሚመረምሩ ሦስት መቶ ሃያ አባሎች ያሉበት ከፍተኛ ምክር ቤት አላቸው፤ 16 የሚያስተዳድራቸውና በበላይነት መንግሥታቸውን በሙሉ የሚጠብቅ አንድ ሰው በየዓመቱ ይሾማሉ፤ ምንም ሳይመቀኙበትና ሳይቀኑበት ሁሉም ለእርሱ ብቻ ይታዘዛሉ። አይሁዳውያን ከሮማውያን ጋር የገቡት (ቃል ኪዳን) 17 ይሁዳ የዮሐንስን ልጅ፤ የአኮስን የልጅ ልጅ አውጶለሞንና የኤልዓዛርን ልጅ ኢያሶንን ስለ ፍቅርና ስለውል እንዲነጋገሩ ወደ ሮም ላካቸው፤ 18 የግሪካውያን መንግሥት እስራኤልን ወደ ባርነት እንደሚጥል በማየት ቀንበራቸውን ለማንሣት ብሎ ነው የላካቸው። 19 መልእክተኞቹ ወደ ሮም ሄዱ፥ መንገድ በጣም ረጅም ነበር፤ ወደ ታላቁ ምክር ግንብ ገቡና እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፥ 20 “ይሁዳ መቃቢስና ወንድሞቹ እንዲሁም የአይሁድ ሕዝብም ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳንና ሰላም ለማድረግ ከቃል ኪዳን ጓደኞቻችሁና ከወዳጆቻችሁ ጋር የትብብርና የሰላም ስምምነት እንድንዋዋል እና የእናንተም ወዳጆች እንድንሆን ፈልገው ወደ እናንተ ልከውናል”። 21 የምክር ቤቱ አባላት በነገሩ ደስ ተሰኙ። 22 እነሆ በናስ ሠሌዳ ላይ በመቅረጽ ጽፈው የሰላምና የቃል ኪዳን መታሰቢያ እንዲሆን ወደ ኢየሩሳሌም የላኩት የጽሑፍ ግልባጭ እንዲህ ይላል፥ 23 “ለሮማውያን ለአይሁዳውያንም ሕዝብ ለዘለዓለም በባሕርና በምድር ብልጽግና ይሁን፥ ሰይፍና ጠላት ከእርሱ ይራቅ፤ 24 ነገር ግን በመጀመሪያ በሮም ወይም የበላይ ጠባቂነትዋ በሚገኝበት በማንኛውም ቦታ ከሚገኙት ከጦር ጓደኞችዋ በአንድ ላይ የሚያስጋ ነገር ቢገኝ 25 የአይሁድ ሕዝብ ከሮም ጋር ሆኖ በሙሉ ልብ ይዋጋል፤ የሚዋጋውም የጊዜው ሁኔታ በሚያስገድደው መሠረት ነው። 26 ከሮም ጋር ጦርነት ለሚገጥሙ ጠላቶች ሮም እንደወሰነችው ስንዴ ወይም የጦር መሣሪያ ወይም ገንዘብ ወይም መርከቦች አይሰጡም፤ ወይም አያበድሩም። በመልሱ ምንም ሳይቀበሉ ግዳጃቸውን ይፈጽማሉ። 27 እንዲሁም አስቀድሞ የአይሁድን ሕዝብ የሚነካ ጦርነት ቢነሣ የጊዜው ሁኔታ በሚያስገድደው መሠረት ሮማውያን ከሕዝቡ ጋር ሆነው በሙሉ ልብ ይዋጋሉ። 28 ሮም እንደወሰነችው ለእስራኤል ጠላቶች ስንዴ ወይም የጦር መሣሪያ ወይም ገንዘብ ወይም መርከቦች አይቀርቡም፤ ሮማውያን ግን በታማኝንት ግዳጃቸውን ይወጣሉ። 29 ከአይሁድ ሕዝብም ጋር ያደረጉት ቃል ኪዳን ይህን ይመስል ነበር። 30 በመጪው ጊዜ እነዚህ ወይም እነዚያ አንዳንድ ነገር መጨመር ወይም መቀነስ ቢፈልጉ እንደ ፈለጉት ያደርጋሉ፤ የተጨመረው ወይም የተቀነሰው ነገር በሙሉ ተቀባይነት ይኖረዋል።” 31 ንጉሥ ዲሜጥሮስ በእነርሱ ላይ ስለመፈጸመው በደል እንዲህ ብለን ጽፈንለታል፥ “ወዳጆቻችንና የጦር ጓደኞቻችን በሆኑት አይሁዳውያን ላይ ሰለምን ቀንበርህን አከበድህባቸው? 32 እንደገና እነርሱ የከሰሱህ እንደሆነ እኛ እነርሱን እናግዛለን፤ አንተን በባሕርም ሆነ በምድር እንወጋሃለን።” |