1 ነገሥት 8:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህናቱ ከቤተ መቅደሱ እንደ ወጡ ደመና የጌታን ቤት ሞላው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናቱ ከቤተ መቅደሱ በወጡ ጊዜ፣ ደመና የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሞላው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህናቱ ከቤተ መቅደሱ እንደ ወጡ ቤተ መቅደሱ ድንገት በደመና ተሞላ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህናቱም ከመቅደሱ በወጡ ጊዜ ደመናው የእግዚአብሔርን ቤት ሞላው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህናቱም ከመቅደሱ በመጡ ጊዜ ደመናው የእግዚአብሔርን ቤት ሞላው። |
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና፥ እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደተቀደሰው ስፍራ፥ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው።
ቤተ መቅደሱ ከእግዚአብሔር ክብርና ከኀይሉ የተነሣ በጢስ ተሞላ፤ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ ማንም ወደ መቅደሱ መግባት አልቻለም።