ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ እጁን አንሥቶ ወደ ነቢዩ በማመልከት! “ያዙት!” የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤ የንጉሡም ክንድ ወዲያውኑ ድርቅ ብሎ ሽባ ስለ ሆነ የዘረጋውን እጁን መመለስ አልቻለም።
1 ነገሥት 22:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም በደኅና እስክመለስ ድረስ በእስር ቤት አስገብተው ደረቅ እንጀራና ውሃ ብቻ እየሰጡት እንዲቆይ ያደርጉ ዘንድ በእኔ ስም ንገራቸው” ሲል አዘዘው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ ‘ንጉሡ፣ ይህን ሰው እስር ቤት አስገቡት፤ በደኅና እስክመለስም ድረስ፣ ከደረቅ እንጀራና ከውሃ በቀር ሌላ እንዳትሰጡት’ ብሏል በሏቸው” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም በደኅና እስክመለስ ድረስ በእስር ቤት አስገብተው ደረቅ እንጀራና ውሃ ብቻ እየሰጡት እንዲቈይ ያደርጉ ዘንድ በእኔ ስም ንገራቸው” ሲል አዘዘው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ በደኅና እስክመለስ ድረስ ይህን ሰው በግዞት አኑሩት፤ የመከራም እንጀራ መግቡት፤ የመከራም ውኃ አጠጡት በሉአቸው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “በደኅና እስክመለስ ድረስ ይህን ሰው በግዞት አኑሩት፤ የመከራም እንጀራ መግቡት፤ የመከራም ውሃ አጠጡት፤” በሉ’” አለ። |
ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ እጁን አንሥቶ ወደ ነቢዩ በማመልከት! “ያዙት!” የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤ የንጉሡም ክንድ ወዲያውኑ ድርቅ ብሎ ሽባ ስለ ሆነ የዘረጋውን እጁን መመለስ አልቻለም።
አሳም በባለ ራእዩ ላይ ተቈጣ፤ ስለዚህም ነገር ተቈጥቶአልና በቊራኛ አስሮ በወህኒ ቤት አኖረው፤ በዚያን ጊዜም አሳ፥ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎችን አሠቃየ።
‘በጌታ ቤት አለቃ ሆነህ እያበደ ትንቢት የሚናገርን ሰው ሁሉ በመንቈርና በዛንጅር አስረህ እንድታኖረው ጌታ በካህኑ በዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል።
ይሁዲም ሦስት ወይም አራት ዓምድ ያኽል ባነበበ ቍጥር፥ ንጉሡ ጸሐፊ በሚጠቀምበት ሰንጢ የተነበበለትን እየቀደደ ክርታሱ በሙሉ ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃ ውስጥ ወዳለው እሳት ይጥለው ነበር።
ኤርምያስንም ወሰዱት፤ በእስር ቤቱም አደባባይ ወደነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጉድጓድ ውስጥ ኤርምያስን በገመድ አውርደው ጣሉት። በጉድጓድም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።
ይህንም ደግሞ በኢየሩሳሌም አደረግሁት፤ ከካህናት አለቆችም ሥልጣን ተቀብዬ እኔ ከቅዱሳን ብዙዎችን በወኅኒ አሳሰርኋቸው፤ ሲገድሉአቸውም አብሬ ተቸሁ።
የቦካውን ቂጣ ከእርሱ ጋር አትብላ፥ ከግብጽ አገር በችኮላ ስለ ወጣህ ከግብጽ አገር የወጣህበትን ቀን በዕድሜህ ሁሉ ታስብ ዘንድ ይህን ቂጣ፥ እርሱም የመከራን እንጀራ፥ ሰባት ቀን ከእርሱ ጋር ብላ።
የሚጠብቅህን መከራ አትፍራ። እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያስገባ ነው፤ ለዐሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።