የሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ መላ ሠራዊቱን በአንድነት ሰበሰበ፤ ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ባሉአቸው ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ተደግፎ በመዝመት የእስራኤል ዋና ከተማ የሆነችውን ሰማርያን ከቦ አደጋ ጣለባት።
1 ነገሥት 20:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ አሁን ሠላሳ ሁለቱን ነገሥታት ከጦር አዛዥነታቸው ሽረህ፥ በእነርሱ ቦታ ሌሎችን የጦር አዛዦች ሹም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ እንዲህ አድርግ፤ ነገሥታቱን በሙሉ ከአዛዥነታቸው አስነሣ፤ በቦታቸውም ሌሎች ሹማምት አድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ አሁን ሠላሳ ሁለቱን ነገሥታት ከጦር አዛዥነታቸው ሽረህ፥ በእነርሱ ቦታ ሌሎችን የጦር አዛዦች ሹም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአክዓብም ወገን በከተማዪቱ ውስጥ የሞተውን ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳውም የሞተውን የሰማይ ወፎች ይበሉታል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአክዓብም ወገን በከተማይቱ ውስጥ የሞተውን ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳውም የሞተውን የሰማይ ወፎች ይበሉታል።” |
የሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ መላ ሠራዊቱን በአንድነት ሰበሰበ፤ ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ባሉአቸው ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ተደግፎ በመዝመት የእስራኤል ዋና ከተማ የሆነችውን ሰማርያን ከቦ አደጋ ጣለባት።
ቤንሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞች የሆኑ ሠላሳ ሁለቱ ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ በመጠጥ ሰክረው በነበሩበት ጊዜ እኩለ ቀን ላይ የእስራኤል ሠራዊት ወጣ።
ባለሟሎቹ የሆኑ ባለ ሥልጣኖች ንጉሥ ቤንሀዳድን እንዲህ አሉት፤ “የእስራኤል አማልክት የተራራ አማልክት ናቸው፤ እስራኤላውያን እኛን ማሸነፍ የቻሉት ስለዚህ ነው፤ በሜዳማ ስፍራዎች ጦርነት ብንገጥማቸው ግን እናሸንፋለን።
ከዚህ በፊት የተደመሰሰውን የሚያኽል ብዙ ሠራዊትና እንዲሁም በቀድሞዎቹ ልክ ፈረሶችንና ሠረገሎችን አደራጅ፤ ከዚያም በኋላ እስራኤላውያንን በሜዳ ተዋግተን ድል እንነሣቸዋለን።” ንጉሥ ቤንሀዳድም በእነርሱ ምክር ተስማምቶ ለመፈጸም ወሰነ።